Sidama Liberation Front

header hb
 

 ከሲዳማ ብሔራዊ ነፃነት ግንባር ስለወቅቱ ሲዳማ ክልልን በሚመለከት የተሰጠ መግለጫ

በኢትዮጵያ ኣሁን ያለው ኣገዛዝ በገዛ ህዝቡ ላይ በተለይም በሲዳማ መንግስታዊ ሽብር በመፍጠር መጠነ ሰፍ የህዝብ ሀብት ዘረፋ በመፈጸም ላይ ይገኛል። ይህ የዘረፍና ነፍሰገዳይ ቡድን በ2019 ኣብይ የሾማቸው የክልሉ ባለስልጣናት በደስታ ሌዳሞ፥ ኣለማየሁ ጢሞትዎስ ና ኣብርሃም ማርሻሎ ኣማካይነት እያስፈጸመ ይገኛል። በ2019 ኣ/ም ኣብይ በፓርላማ ፍት ወጥቶ የሲዳማን ህዝብና የክልል ጥያቄ እንቅስቃሴ በተመለከተ ለቀርበለት ጥያቄ መልስ ስሰጥ ‘ሲዳማን እንደሱማሌ በወታደራዊ ሀይል እደመስሳለሁ “ ብሎ ቃል ገባ። በኣለውም መሰረት 18 ጁላይ 2019 የፈደራልና የደቡብ የታጠቁ ሀይሎችን በማሰማራት 153 ያልታጠቁ የሲዳማ ወጣቶችን በተጠና መልክ ጨፈጨፈ። የዚህ ግፍ ተዋናይ የነበረችው ሰላም ሳይኖራት የሰላም ሚንስትር ተብየዋ ና የዴህዴን ሊቀመንበር ሙፍሪያት ካሚል ነበረች። ለዝህ እኩይ ግባራቸው ተባባርዎች በውስጥ ግድያውን ያስፈጸመችው በሲዳማ ክልል ባሰማራቻቸው ሰላዮች ና ጆሮ ጠብዎች ኣማካይነት ነበረ። ወ/ሮ ሙፍሪያት ካሚል ሲዳማ ጠል የሲዳማ ክልል ጥያቄ ለማክሸፍ በግንባር ቀደም የተሰለፈች ስትሆን የክልሉንም ረፈረንዱም ለማሰናከል ጉዳዩን የጸጥታ ጉዳይ በማድረግና በስውር ግለስቦች ላማስገደል የስለላ መዋቅር በመዘርጋት ገንዘብ በማፍሰስ ያሰረችው ሴራ ሳይሳካላት ተዘጋ። በወቅቱ ሆነ ዛሬ የሙፍሪያት ሰላዮች ሆነው እያገለገሉ ያሉት 1ኛ ድስታ ሌዳሞ 2ኛ/ ኣለማየሁ ጢሞትዎስ ነበሩ/ናቸውም። እነዚህ የታሪክ ኣተላ የሆኑ ከሀድዎች ከህዝባችን ግድያ ባሻገር የህዝቡ ግፍት ረፈረንደም ተካህዶ ሲዳማ ድል ስያደርግ እነዚህ ከሀድዎች የህዝቡን የመምረጥ መብት በመጋፋት በሲዳማ ህዝብ ላይ በጉልበት ተሾሙ። ይህም የተደረገው ኣድሱን ክልል ኣዳክሞ ሌሎችን የክልል ጥያቄ ኣንዳያነሱ ማስፈራሪያ ለማድረግ ነው። በዝህም የኣብይ ኣላማ ግብ መቶለታል። ዛሬ የሲዳማ ክልል የመጨረሻ የወደቀ ፥ በዘራፍዎችና በውስጥ በተደራጁ የማፍያ ቡድኖች እጅ ወድቇል። የሲዳማ ኣመራር ተብዬው በደስታ ሌዳሞ፥ ኣለማየሁ ጢሞትዎስና ኣብርሃም ማርሻሎ የምመራው መንግስታዊ ሽብር በህዝቡ ላይ ኣውጀዋል። ይኽውም

1ኛ/ የመንግስትና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅት ሰራተኞችን ያለፍርድ ትእዛዝ ይታሰራሉ፥ ፍርድ ቤት ኣይቀርቡም፡ ይገረፋሉ፡፥ ንብረታቸውን ይቀማሉ። በዝህም ከፍተኛ የስብኣዊ መብት ጥሰት ይፈጸማል።

2ኛ/እድሜያቸው ለትምህርት ያልደረሱ ወጣቶችንና እስረኞችን በማስፈራራት ለወታደርነት በመመልመል በትግራይና ኦሮሚይ ለምደረገው ህገ-ወጥ ጦርነት በመላክ ለማያምኑበት ኣላማ እንድማገዱ ኣድርገዋል። ይህ ጦርነት የኢትዮጵያን ህብረብሄር ፈድራሊዝም ሀገመንግስት ለማፍረስና ሀገመንግስቱን ለመሻር የምደረግ በመሆኑ ሲዳማ ወጣት ይህንን ኣላማ ኣይደግፍም ፥ ለመሻር የተነሱትን ሀይሎችን የታገላቸዋል።

3ኛ/ ዛሬ ሲዳማ እንደ ናዝ ጀርመን የኣይሁዶች ማጎሪያና መጨፍጨፍያ ካምፕ -ኣሽዊትስ( Auschwitz) ኣይነት የትግራይና ኦሮሞ ብሄረስብ ኣባላት ማስሪያና ማሰቃያ ሆናለች። ይህም ከመነሻው የሲዳማ ጠል የሆኑ ሀይሎች የሲዳማን ህዝብ ታሪክ ለማጠልሸት የምፈጽሙት ሴራ መሆኑን የሲዳማና ኣለማቀፍ ህብረተሰብ እንድያውቀ ይደረጋል፡ የሲዳማ ብሄርዊ ነጻነት ግንባር ኣጥብቆ ያወግዛል።

4ኛ/ የሲዳማ ህዝብ ለ130 ኣመታት የታገለለትን የራስ ገዝ መብት በመጣስ የፍትህና ኢኮኖሚ ፥ የመናገርና የመደራጀት መብቶች ታፍነዋል፥፡ የኢኮኖሚና የፖለቲካ ነጻነት ኣጥቶ ታፍኖ እየተንገላታ ይገኛል። ከመንግስታዊ ሽብር ፈጠራ ባሻገር እነደስታ ሌዳሞ፥ ኣለማየሁ ጢሞትዎስና ኣብርሀም ማርሻሎ የኣዋሳን መሬት በመሸጥ የታውቁ ናቸው።በዝህም ከራሳቸው ቤተስቦች ባሻገር ለደጋድፍዎቻቸው መሬቱን በማከፋፈል ላይ ተጠምደዋል። ይህ የመሬት ዘረፋ የኢህኣዴግም ሆነ ስሙ ቀይሮ የመጣው የብልጽግና በሽታ ነው። ኣለማየሁ ጢሞትዎስ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ያልጨረስ ሲሆን ለዝህ ያበቃው የሲዳማ ጠልነቱ ሲሆን ይህ ግለሰብ 11 ሚልዮን ከቦርቻ የዘረፈ ና ከኣብርሀም ማርሻሎ ጋር የኣባያ ዙርያ ወረዳ መሬት የሸጡ ምንም እውቀትት የሌላቸው በሙፍሪያት ኣይዞ ባይነት የሚነዱ የሲዳማ ህዝብ የመከራው ምንጭ ናቸው።

ዛሬስ ሲዳማ ምን እየሆነ ነው? ዘራፍዎች ራሳቸውን ብልጽግና ብለው ስሰይመው የሲዳማ ባጀት ከ10 ቢልዮን በታች ነበረ። ይህንን ባጀት ነው ህብረብሄር ፈደራሊዝምን ለማውደና ኣሀዳዊነትን ለመትከል ለምደረገው ጦርነት ፥

1ኛ/ 10 ሚልዮን ለኣማራ ብልጽግና

2ኛ/ 40 ሚልዮን ለኣፋር ብልጽግና

3ኛ/ 5 ሚሊዮን ከኣዋሳ ዩንቭርሲቲ ለመከላከያ ስጦታ ኣድርገዋል።

4ኛ/ ኣሁን ደግሞ ሲዳማ ክልል በሰሜን ሸዋ ኣማራ ዞን ፈርሶኣል ለተባሉ ጤናጣቢያዎች መልሶ ለመገንባት ሙሉ ሀላፍነቱን ወስዶኣል። በሲዳማ ሆስፒታሎችና ጤና ጣቢያዎች ኣስፒርን እንኳ የላቸውም።

5ኛ/ በክርስትና ስም የህዝብ ገንዘብ በመቀማት ራሳቸውን ኣበልጻግ በመሆን ከታወቁት ነቢያትና ሀዋሪያት ነን ከምሉት ኣንዱ ለሆነው ዮናታን ኣክልሉ 1 ሚሊዮን ብር ደስታ ሌዳሞ መስጠቱ ይታወስ ነው። ይህ ግለሰብ በኣዋሳ በወላይታና ሲዳማ ወጣቶች መካከል የሲዳማን ክልልነት ጥያቄ ረፈረንደሙ ለማስተጓጎል ግጭት ለመፍጠር ሞክሮ የከሸፈበት ግለሰብ ነው።ዛሬ የሲዳማ ወጣት ና ህዝብ በተለያዩ ችግሮች ተወጥሮ ባለበት ወቅት ያን ሁሉ የሲዳማን ንብረትና ሀብት ማስተላለፍ ለግብር ከፋይ ያለቸውን ንቀትና ማናለብኝነት ሲሆን ለዝህ ሁሉ ገንዘብ ተጠያቂ እንደሚሆኑ የሲዳማ ብሄራዊ ነጻነት ግንባር ያሳውቃል። ስለሆነም

1. በመንግስት የሚደረገው የህዝቡን ሰላማዊ ህይወት ማናጋት ማደህየት ማሰር ግፍ መፈጽም በሲዳማ በኣስቸኳይ እንድቆም

2. ረ/ፕሮፈሰር ተሰማ ሾሌና ሌሎች እስረኞች በኣስቸኳይ እንድፈቱ ። ለተፈጸመው ግፍ በደል ለደረሰባቸው ካሳ እንድከፈላቸው እንጠይቃከን።

3. የሲዳማ ብሄራዊ ነጻነት ግንባር በሲዳማ ለተፈጸሙት ግፎችና ዘረፋዎች ተጠያቅዎች ደስታ ሌዳሞ፥ ኣብርሀም ማርሻሎና ኣለማየሁ ጢሞትዎስ ሲሆን እነዚህም ከ ስልጣን እንድወርዱና ለፈጸሙት ወንጀል ተጠያቅ እንድሆኑ

4. የሲዳማ ህዝብ ገንዘብና ሀብት ዝውውር በኣስቸኳይ እንድቆም የባከነውን ኣባካኞች እንድክፍሉ።

5. የሲዳማ ክልል የግፍ ማስፈጽሚያ መሆኑ በኣስቸኳይ ኣንድቆም ና በክልሉ ለተፈጸመው ወንጀሎች ተጠያቂዎቹ ኣብይና 3ቱ የሾማቸው ባልስልጣናት መሆናቸውን እንድታወቅ።

6. ኣለም እቀፍ ህብረተስብ የሲዳማ ክልል የምደረገውን ግፍ ኣውቆ ኣንድከታተል ሲዳማ ብሄራዊ ነጽነት ግንባር ይጠይቃል።ይህ ግፍ የሚመለከተው የብልጽግና ፓርቲና ተባባሪዎች ብቻ መሆናቸውን እንድታውቅ እንወዳልን።

ድል ለሲዳማ ዲሞክራቲክ ሀይሎች

ድል ለህብረብሄር ፈደራሊስት ሀይሎች

የሲዳማ ብሄራዊ ነጻነት ግንባር

30 ዲሰምበር 2021