Sidama Liberation Front
header hb
 
   ከፈደራልስት ሃይሎች ጥምረት የትግል አጋርነትን በተመለከት
   ከሲዳማ ብሄራዊ ነጻነት ግንባር የተሰጠ መግለጫ

ነሃሴ 17፣ 2013 

አሁን ያለችዉ ኢትዮጵያ የህዝቦችዋን ደህንነት መጠበቅ ያልቻለች፥ በመንግስት ሀይሎች የዘር ፍጅት የሚካሄድባት  በ21ኛው ክፍለ ዘመን የጨለመተኛ ኣምባገነኖች  ኣገር ሆናለች። በኣገርቷ እየተፈጸመ ያለው ግፍ በመጠኑና በኣይነቱ የተለየና ኣሁንም የቀጠለ የግፈኛው ኣሀዳዊው ስርኣት ውጤት ነው፡፡

እሀዳዊነትና ኣሀዳውያን የኣገርቷ ብሄር ብሄረስቦችን ጸር የሆኑ ከጦርነት በስተቀር ሌላ ራእይ የለላቸው የቀማኛና የዘርፍ ስብስቦች ናቸው።ዛሬ በተጋሩ፥ በኦሮሞ ፥በኣፋር፥ በቤናሻንጉል፥ ቅማንትና ኣገው ላይ ቀደም ብሎም  በሲዳማ በኮንሶ ፥በሱማሌና ወላይታ ህዝቦች ላይ ተመሳሳይ ግፎችን ፈጽሞኣል።ኢትዮጵያ ወደመበታተን ደረጃ ደርሳለች።

መንግስት ተብየው የወጠነው ሴራ ብሄራዊና ሉኣላዊነታችንን የጣሰ በተጋሩና ኦሮሞ ህዝቦች ላይ እየተፍጸመ ያለውን  የዘር ፍጅት ለማቆምና ኣገርቷን ከመበተን ለማዳን  የሲዳማ ብሄራዊ ነጻነት ግንባር ትግሉን ከኦሮሞ መከላከያ ሰራዊት-ኦነግ ሰራዊትና ትግራይ መከላከይ ሀይልን ተቀላቅሎኣል። በዝህም  የኣብይ ቀለብተኞችን ፍጻሜ በማፋጠን  የተከበረች የህዝቦችዋ መብትና ጥቅም የሚከበሩባትን ህብረብሄር ፈደራሊስት ኢትዮጵያን ለመገንባትና ኣሀዳዊነትን ለኣንደና ለመጨረሻ ለመቅበር ቆርጠን ተነስተን ትግሉን ኣቀጣጥለናል። ከኣሁን ወድህ ለኢትዮጵያ ችግር ፈችው ሁሉን ኣቅፍ የሽግግር መንግስት ብቻ መሆኑንና በኣጽኖት ለብሄርብሄረስቦች መልእክታችንን እናስተላልፋለን።


ድል ለኢትዮጵያ ብሄር ብሄረስቦች!


የሲዳማ ብሄራዊ የነጻንት ግንባር