Sidama Liberation Front

header hb
 

ከሲዳማ ብሔራዊ ነፃነት ግንባር SNLF በወቅታዊ በሲዳማ ህዝብ ታርክ በሆነው ሲአን ላይ ግሌሰቦች  እየወሰዱ ባሉት ክህደትና ጥፋትን  በአስቸኳይ እንዲያቆሙ የተሰጠ መግለጫ

2 ጃንዋር 2021

ኢህአዴግ  ድርጅት ከሁለት አመታት ወዲህ ውስጤን አድሻለው ፣ ተለውጫለው ፣ስሜንም ቀይሬያለው በማለት ፣በሌላ በኩል ግን ህዝቡን ሲጨቁኑ ከነበሩ ድርጅቶች አብላጫውን ክፋይ ማለትም ከአራቱ የኢህአዴግ ድርጅቶች ሶስቱ እንዲሁም ህዝብ ላይ ጦርነት አውጁ ሲባሉ ሲያውጁ ፣እሰሩ ሲባሉ ሲያስሩ እና ግደሉ ሲባሉ ሲገድሉ የነበሩ  ነባር አመራሮቹንም ጭምር በመያዝ በህዝቡ ላይ ተመሳሳይ በደል ሲያደርሱ ጦርነት በመክፈት ፣በርካቶችን በማሰር እና በማሰቃየት ከፍተኛ በደል ሲያደርሱ ይገኛሉ ። የሲዳማ ህዝብ ለዘመናት ሲጠይቅ የነበረውን ራስን በራስ የማስተዳደር እና የክልል አደረጃጀት ጥያቄ በማስተጋባታቸው እና ከዚሁ ጋር በተያያዘ ባለፉት ሁለት አመታት ከሶስት መቶ ያላነሱ ንጹህ ውድ የሲዳማ ልጆችን ተነጥቀናል ። በረካቶች ለወራት ታስረው ለከፍተኛ ማህበራዊ እና ስነልቦናዊ እንዲሁም ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ተዳርገዋል። የሲዳማ ህዝብ የሚደርስበትን በደል ለሌላው ህዝብ እና አለም አቀፍ ማህበረሰብ እንዲያሰማ ታልሞ ውጭ በምንኖር የሲዳማ ተወላጆች እና የሲዳማ ህዝብ ድጋፍ የተቋቋመው የህዝብ ድምጽ ኤስ ኤም ኤን ዛሬ የመንግስት ሚዲያ ሆኖአል።ክልሉም የሲዳማ ክልል ከመባል ውጭ የህዝብ መብት የማይታይበት ከስሙ ውጭ በዞኖች ገና ያልተዋቀረና  ክልሉ እንድፈርስ በሚደረገው አሀዳዊ መንግሥት ውስጥ የመጀመሪያ ሆኖ  ተፈፃሚነትን ብቻ እየጠበቀ ወንጀለኞ ቀማኛና ዘራፍ በማደራጀት የኣሀዳዊውይን ፍላጎት ማስፍጸምያ ሆኖኣል፥በቀን በጠራራ ፀሐይ ለፖለቲካ ጥቅም ዘራፊ የግለሰቦችን አደራጅቶ የሚመራ ክልል ነው።ወንጀሉ ተራ  የእጅ ስልክ በመቀማት በማስፈራራት በማሰር   ከኣሀዳዊ ስራት በባስ ሁኔታ ትውልድን እያጎሳቆሉ ናቸው።

መላው የአገራችን ህዝቦች እንዲሁም አለም አቀፉ ማህበረሰብ የአገሪቱ ቀጣይ እጣ ፈንታ አደጋ እያሳሰበው በሚገኙበት፣ ገዥው መንግስት ተቃዋሚ የፓለቲካ መሪዎችን እንዲሁም ሚዲያዎችን በመዝጋት  ጋዜጠኞችን  በማሰር ፣ለከፍተኛ የህዝብ  ግጭት እና መፈናቀል ምክኒያት እየሆነ በሚገኝበት ፣ አብዛኛው የአገሪቱ አከባቢዎች ላይ የደህንነት ስጋት በነገሰበት  በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ጥቂት የሲአን አመራር አባላት ታሪካዊውንና ብቸኛ የሲዳማ የትግል ታሪክ ማንነት የተሸከመውን እና ከብዙ ድካም ጋርም ቢሆን የህዝብ ድምጽ ሆኖ የቆየውን ድርጅት ደብዛውንና አሻራውን ለማጥፋት ሴራ ሲጎነጉኑ ቆይተዋል  ። ለዚህም መደላደል ለመፍጥር ያመቻቸው ዘንድ ያለምንም ውይይት እንዲሁም ከገዥው ድርጅት ጋር የመርህ የግብ ልዩነት መኖሩን እያወቁ  ጥቂት ግለሰቦች ስልጣን እና ጥቅማጥቅም ተቀብለው የትግሉን ኣቅጣጫ ለማስቀየር ሙከራ ኣድረገዋል። ይህንን እኩይ ተግባር የሲዳማ ህዝብ እና አባላቱ እንዳላየ ያለፉበት የራሱ ምክንያት ቢኖረውም ዝምታውን ግን ከህዝቡ እና አባላቱ የፓለቲካ ንቃተ ህሊና ጋር በማያያዝ ወደ ቀጣዩ ድብቅ ምእራፍ ተሸጋግሮ ከሲዳማ ህዝብ የራስ አስተዳደር ፍላጎት ጋር ፈጽሞ ተጻጻሪ  ከሆነው እና የህዝቡን ፍላጎት ለማፈን ስጥር ከከረመው ብልጽግና ጋር አላስፈላጊ ትብብር ለማድረግ አጀንዳ ቀርጾ ሲዳማን ለመሸጥና ሲአን የሚባል ድርጅትን ዓላማ. ታርክ በሙሉ የብልጽግና ለማድረግ ቀን ቆርጦ ይገኛል። ለሲዳማ ህዝብ ጠበቃና እውነተኛ ታጋይ የሆኑትን በማሳደድ ጨምሮ አንጋፋ የህዝብ ልጅ ና ታጋይ  አቶ ጰጥሮስ ዱቢሶን የሀዋሳ አከባቢ የሲአን አመራሪን   ከማዕከላዊ ኮሚቴ ከማባረር አልፈው ህዝብን የማይወክሉ ጥቅመኞች ዛሬ መንግስት ተገን በማድረግ የህዝብን ታርክ ለመሸጥ ወስነው ይገኛሉ።

የሲዳማ ህዝብን ፍላጎት ከክልል አደረጃጀት ባሻገር  መመልከት የተሳናቸው ግለሰቦች እንዲሁም አደረጃጀት ራስን በራስ ለማስተዳደር የሚያስችል መዋቅር እንጂ በራሱ ግብ እንዳልሆነ በቅጡ ያልተረዱ ግለሰቦች የድርጅቱ አመራር ውሰጥ በመሰግሰግ ድርጅቱን እና ህዝቡን ዋጋ ለማስከፈል እየተጣደፉ ይገኛሉ ።በደኢህደን ውስጥ የከራረሙ እና በአሁኑ ጊዜ የብልጽግና ፓሪት አመራር የሆኑ የሲዳማ ክልል ወንጀሌኞችና የዛሬ አመራሮች በክልሉ ሲዳማን ወካይ አማራጭ ድምጽ እንዳይኖር የልዩነት አላማ የያዙ ግለሰቦችን እና ድርጅቶችን በሲዳማ ለማክሰም እና ለማጥፋት ከፍተኛ እንቅስቃሴ እያደረጉ መሆኑ ከህዝብ የተሰወረ አይደለም። በተለይም በብሄር ስም የተደራጁ የፓለቲካ ድርጅቶችን በህግ ማገድ ህዝባዊ ቁጣ ሊቀሰቅስብኝ ይችላል ያለው የብልጽግና  ድርጅት በየአከባቢው የሚገኙ ድርጅቶችን የፖለቲካ ፓርቲዎችን ግማሹን አመራሮችን በማሰር እና አባላትን በማስፈራራት በማዳከም ፣ ድርጅቶቹን በመከፋፈል ፣ሌሎችን ደግሞ ወደ ራሱ እንዲቀላቀሉና ታሪካቸውና ትግላቸው በአጭሩ እንዲቀጭ የማድረግ ስራ ስሰራ ሰነባብቷል። በወቅቱ ካላለቁለት ስራዎች አንዱ ለበርካታ ዘመናት የሲዳማን ህዝብ በማታገል የቆየውን  ሲአን ክልሉን እንዲያስተዳድር ህዝቡ እድል ሊሰጠው ስለሚችል ድርጅቱን ሙሉ በሙሉ ደብዛውን ማጥፋት የሚል ዕቅድ ይገኝበታል ።  መንግስት ሲአንን በዚህ ደረጃ እንዲፈራ እና ትኩረት ሰጥቶ ለማፈራረስ ከተነሳባቸው ምክኒያቶች ውስጥ አንዱ ድርጅቱ የሲዳማ ሁሉ የልብ ንግግርና የደሙ የነፍሱ ብሎም የሲዳማ ሁሉ ታርክ በመሆኑና የሲዳማ ትግል ታርክ ቀሳቃሽ የጀርባ አጥንት ሲዳማነት አንድነት በመሆኑ በሌላም ከኦሮሞ ነጻነት- ኦነግ ጋር ካለው ታሪካዊ የትግል ግኑኝነት ጋር ይያያይዙታል። እነዚህ ሁለት ድርጅቶች በየፊናቸው በሚወዳደሩባቸው ክልሎች ከፍተኛ ድምጽ የሚያገኙ ከሆነ በአማራ ፣ ትግራይ፣ሶማሊያ እንዲሁም በሌሎች ክልሎች የተደራጁ ብሄራዊ ድርጅቶች የሚኖራቸውን ድምጽ ደምረው መንግስት ልመሰርቱ እና ገዥውን ብልጽግና በተደራጀ በአጭር እድሜ ከከሰሙ መንግስታት አንዱ ልያደርገው እንዲሁም እስካሁንም ለፈጠረው ቀውስ ተጠያቂ ልያደርገው ይችላል የሚል ስጋት ነው። በዚህ ምክንያት የተሸረበውን የፓለቲካ ሴራ መመልከት ተስኖኣቸው ለጊዜያዊ የስልጣን እና ገንዘብ መደለያ ድርጅቱንና የድርጅቱን ህዝባዊ አላማ ለማጥፋት አጀንዳ ቀርጸዋል። ሲዳማ መብቱን የሚቀዳጀው በታገለው ድርጅቱ ሲኣን ኣርማ ስር እንጅ በነፍሰገዳይ ልጆቻችንን በበላው ድርጅት ስም ኣይደለም።

የሲዳማ ህዝብ የክልል ጥያቄ ግቡ እኩልነት ፣የኢኮኖሚ ፥ የፖለቲካና ማህበራዊ ፍትህ  መሆኑን ጠንቅቆ የሚያውቅ ህዝብ ነው። እነዚህን ግቦች ለማሳካት ድርጅታችን ሲአን ወቅቱን ያገናዘበ ፕሮግራም እና የመርህ አጀንዳ ቀርጾ ክልሉን በምርጫ ለመረከብ ከፍተኛ ዝግጅት ማድረግ ይጀምራል የሚል ተስፋ በህዝቡ ውስጥ በተፈጠረበት በዚህ ወቅት በፓለቲካ ሴራ ውስጥ መዘፈቅ ፈጽሞ ተቀባይነት አይኖረውም። ለዚህ ደባ ድርጅቱን እየዳረጉ የሚገኙ  ግለሰቦች  ከህዝባዊ ተጠያቂነት አያመልጡም ። ሲአን የህዝብ ነው ። ህዝብ ራሱን በራሱ እንዲያስተዳድር ሲያታግል ፣በርካቶች የመስመሩን አላማ ተከትለው ህይወታቸውን የገበሩበት ድርጅት ነው። ከሲዳማ ህዝብ ጋር ጥብቅ የስነ ልቦናና የፓለቲካ ታሪክ ያለው የአላማ ድርጅት ነው። የሲዳማ ህዝብ ራሱን በራሱ የሚያስተዳድረው በራሱ ቋንቋ የሚናገሩ ነገር ግን የሌሎችን አላማ በሚፈጽሙ ግለሰቦች በመመራት ሳይሆን ከህዝቡ ፍላጎት እና ታሪክ ጋር ቁርኝት ባለው ድርጅት ሲመራ እንደሆነ እናምናለን ;; በተለይ አቶ ዱካሌ ለሚሶ መላውን ሲዳማን ለእፍረትና ለባርነት ለመሸጥ የእራሱን ነፃነትና መሬት ብሎም ማንነት ያልተገናዘበ በእጅ ያለውን የእራሱን ንብረት መሬት ተሰጠኝ በሚል ሰበብ ሲዳማ የሸጠ ይሁዳ ታርክ ብቻ ሳይሆነ ኖሮሞ ሞቶም በግልጽ ቋንቋ የመላው የሲዳማ ህዝብ ደመኛ መሆኑ ግልጽ ነው። እሱም ሆነ የሱ የሆኑ በሲዳማ ውስጥ ስምና ታርክ ቦታ እንደማይኖረው አውቆ  ከቻለ በአስቸኳይ ከዚህ ሰይጣናዊ ሥራ መውጣት አለበት። ይህ በብዙ ደምና ነፍስ የተጻፈ የህዝብ ታርክ በብጣሽ ቁራጭ መሬት የሚለወጥ አይደለም።ስለሆነም የሲዳማ ህዝብ የጨለማውን ዘመን አታግሎ እዝህ ያደረሰውን ድርጅቱን ማፍረስ ማለት ህይወታቸውን የሰውቱን መርሳት ብቻ ሳይሆን ከመቃብር አውጥቶ መሳለቅና ተመልሶ ለነፍጠኛ  መንበርከክ መሆኑን ተንቅቀን እናውቃለን። ኣብይ ህብረብሄር ፈደራሊዝምን ለማፍረስ  በየሰፈሩ የፈጠራቸው ግጭቶች ተመልሰው ራሱን እየበሉት ናቸው። የኣብይ ሴራ በምርጫ ብልጽግና ብቻ ኣሸንፎ ህገመንግስቱን ለመቀየር ኣድፍጦ እየሰራ ሲሆን ግን ያሰበውን ለመፈጽም ሰኣት የለውም።  

ከዝህ ሁሉ በፍት መታወቅ ያለበት  የነፍጠኛ ተላላኪዎች ግንባር ቀደሞች  ደስታ ሌዳሞ፥ አለማየሁ ጥሞቲዎስ፥ አብርሃም ማርሻሎ፥ እንድሁም  በተለየ ሁኔታ ከፖለቲካ ግፍ ወጣ ባለ ደመኞቹን የሲአን አመራር ዱካለ ላሚሶ ፡ለገሰ ላንቃሞና  ደሳለኝ ጋርሳሞ ጋር ምንም ድርድር ሆነ ንግግር ሊኖር አይችልም። የሲዳማን ማንነት የሸጡ በሲዳማ የዘላለም ጠላትነት የተፈረጁ ይሆናሉ። ከጥፋታቸው ካልተመለሱ  ትወልድ  የሚጠይቃቸው ጉዳይ ነው። እነዝህ የህዝባችን ግንባር ቀደም ጠላቶች ናቸው።

ይህ ሳይሆን ቀርቶ ድርጅቱን ለጥፋት የሚዳርግ አደጋ ካጋጠመው  የሲዳማ ህዝብ ትግሉን በድርጅቱ ማእቀፍ በውጭም ሆነ በውስጥ የሚቀጥል መሆኑን አውቃችሁ ድርጅቱን ለህዝቡ በአስቸኳይ እንድታስረክቡ ጥር እናደርጋለን።ይህ የመምራት ታሪካዊ ሃላፊነት እጃችሁ ላይ የወደቀ ግለሰቦች ታሪካዊ ስህተት እንዳትሰሩ በጥብቅ እናሳስባለን ።

ድል ለሰፊው ሲዳማ ህዝብ ይሁን!!!

ሲዳማ ብሔራዊ ነፃነት ግንባር SNLF

ቀን 02 /01/2021