Sidama Liberation Front

header hb
ከሲዳማ ብሄራዊ ነጻነት ግንባር በሲዳማ ስለኣለው ስብኣዊ መብት ጥሰትና ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ የተሰጠ መግለጫና የትግል ጥሪ

ከምንልክ ጀምሮ እስከ ኣብይ እህመድ ያለው የኢትዮጵያ ታሪክ የሚያሳየን ስልጣን ይዘናል ብለው ምንልክ ቤተመንግስት የሚገቡት ሁሉ ባንዳዎችን ሰብስበው ሕዝቡን እየጨፈጨፉ ታሪክ ሰራን፥ የኣባቶቻችንን ኣደራ ተከትለን፥ የኣገርቷን ኣድነት ኣስጠብቀን ለመጭው ትውልድ እናስረክባለን እያሉ በህዝብ ላይ ፋሽታዊ ግድያዎችን እየፈጸሙ ኣልፈዋል። ኣሁን ያለውም የኣቢይ ፋሽስት መንግስት ተመሳሳይ ብቻ ሳይሆን ኣገርቷን ወደማትወጣበት ገደል ከቶኣታል። የግዜ ጉዳይ እንጂ የህዝቦች ትግል የፈጀውን ጊዜ ይፍጅ እንጂ ያሸንፋል።ይህንን መረዳት ያቃታቸው በኣብይ ገንዘብና ሹመት የሰከሩ ሩቁን ማየት የተሳናቸው በሲዳማ ትግል ታሪክ ውስጥ ኣስታዋጽዎ የሌላቸው ጎርፍ ኣመጣሽ እነደስታ ሌዳሞ፥ ኣብርሃም ማርሻሎ ፥ ኣለማዬሁ ጥሞትዎስና ጸጋየ ቱኬ የተባሉት ስነልቦናቸው የተሰለቡ ልጆቻችንን ለኣብሲንያ ፋሽስቶች መሳሪያነት ሸጠው ኣስገድለዋል።እያስገደሉም ናቸው።በተለይም እነዝህ ኣራቱ ግለስቦች ቀደም ብለው በደኢህዲድን ሊቀመንበር በነበረችው ወ/ሮ ሙፍሪት ካሚል ተመልምለው የሲዳማን ክልል ጥያቄ ለማክሸፍ የሰሩና በ2019 ለተገደሉት 153 ወጣቶች ተጠያቅዎች ናቸው።ከዝያም ኣልፎው ለህዝቡ ልማት የተመደበውን ባጀት በሚልዮኖች ኣንስተው ለኣማራ ክልልንና የኣማራ መሬት ኣስመላሽ ሰራዊት በመስጠት የስራ ኣጡን ወጣት ህይወት የጨለመ ኣድርገውታል። ሌላው ኣማራ ራሱን ለመጪው ግዜ እያደራጀና እያስታጠቀ ባለበት ወቅት ኣርቆ ማየት ያቃታቸው በወያኔ ላይ ኣማራ በምነዛው ፕሮፓጋንዳ ተታለው ህዝባችንን ለዳግማዊ ባርነት ለመሸጥ የምንልክ ዘመቻ ተቀላቅለዋል። ዛሬ የሲዳማን ክልል ችግሮች ያነሱትን ምሁራን ለማንበርከክ እስራት እየተፈጸመ ይገኛል። ተልእኮቸው ህብረብሄራዊ ፈደራሊስት ሀይሎችን ኣዳክመው ኣሀዳዊ ስርኣት መልሶ ለመትከል ለየት ያለ ኣስተሳሰብ ያላቸውን በማሰርና በማሰቃየት በህዝብ ስቃይና መከራ ትግሉን ያኮላሹ እየመሰላቸው የምፈጽሙትን ሴራዎች ህዝቡ በግልጽ ልያውቃቸው ይገባል። የምያሳዝነው ሌላው ጉዳይ እበላባይና ኣድርባይ ምሁር የኣዋሳ ዩንቭርስቲ ፕረዝዳንት ኣቶ ኣያኖ በራሶ ለዩንቭርስቲው ምርምርና ጥናት የተስጠውን 45 ሚልዮን ብር ለመከላከያ ማጠናከርያ ብሎ መስጠቱ በጣም ኣስነዋርና ሀላፍነት የጎደለው ተግባር ነው።

በኣሁኑ ሰኣት በደስታ ሌዳሞ የምመራው የዘራፍዎችና የባንዳዎች ቡድን በሲዳማ የኣዋሳ ዩንቭርስቲ ረ/ፕሮፈሰር የሆኑትን ኣቶ ተሰማ ኤልያስን ከመኖሪያ ቤታቸው ሌሊት ኣፍነው ወስደው በኣዋሳ ኣዲስ ከተማ የሌቦች ማጎሪያ እስር ቤት ቀደሞ የሲዳማ ታጋዮችን ማሰቃያ በሆነና ስብኣዊነት በጎደለው እስረኛ ኣያያዝ በዜጋው ላይ ግፍ እየፈጸሙበት ይገኛሉ። ፍትህና ዳኝነት የጎደላቸው ፋሽስቶች ለህዝብ መብት በቆሙት ላይ የምፈጽሙት ተግባር የማንነታቸው መገለጫው መሆኑ ለሁሉም ዜጋ ገልጽ መሆን ኣለበት። ሲዳማ ህዝብ የታገለው ለፍትህ፥ ለዲሞክራሲና ለነጻነቱ ሲሆን እውቀተቢሶች ይህንን የትግል ኣቅጣጫ ለመቀልበስ የነፍጠኛው ኣሽከር በመሆን ህጻናትን ለወታደርነት በግዳጅ እየመለመሉ፥ተማሪዎችንና መምህራንን በማስፈራራትና በማሰር ላይ ናቸው።ከዝያም ኣልፈው ትናንት 153 ወጣቶቻችንን ለኣስገደለው ኣጎብድደው የኣብይን ስልጣን ዘመን ለማራዘም ሽር ጉድ ስሉ ማየት በጣም ኣሳፋርና ወንጀልም ነው። ከዝህም ሌላ በኣሁኑ ሰኣት በሲዳማ ክልል የምካሄደውን ዘረፋና የመብት ጥሰቶችን ይቃወማሉ ተብለው የተጠረጠሩትን 17 ግለስቦችን ስም ዝርዝር ኣዘጋጅተው ለማሰር እያሳደዱ ይገኛሉ። የሲዳማ ህዝብ ይህንን ሁሉ በዝምታ ኣይመለከተውም ፥ በመሆኑም የእንዝህን እኩይ ተግባራትን ለማክሸፍ ከብልጽግና ውጪ ያላችሁ ምሁራን፥ወጣቶች(ወንድ ሆነ ሴት) የሲዳማ ሽማግሌ ሆነ ገበሬ ከዝህ በታች የቀረቡት የክልሉ ኣንገብጋቢ ጥያቄዎች እንድመለሱ ትግሉን እንድትቀላቀሉ የሲዳማ ብሄራዊ ነጻነት ግንባር ጥሪ ያቀርባል፥፡ ይኽውም

1ኛ/ ረ/ፕሮፈሰር ተሰማ ኤልያስ በኣስቸኳይ ተፈቶ ወደስራው እንድመለስና የሞራል ካሳ እንድከፈለው።

2ኛ/የሲዳማ ምሁራንና የሌሎች በተለይ 17 ግለሰቦች እየተፈለጉ ያሉት የማሳደድና የማሰር ተግባራት ህገወጥ በመሆኑ በኣስቸኳይ እንድቆም።

3ኛ/ሌላው የሲዳማ ህዝብ ማወቅ ያለበት የሲዳማ ኣመራር ነን ተብየዎቹ የኣብይ ፋሽስቱ ኣሽከሮች በኣሁኑ ሰኣት ኣቦስቶ ከተማ ባለው ፖሊስ ማሰልጠኛ ከተቋቋመበት ኣላማ ውጭ 1400 የትግራይ ተወላጆች ማጎሪያ ኣድርገው ግፍ እያስፈጸመ ይገኛል። ይህ ግፍ መፈጸም ተግባር የሲዳማን ህዝብ እሴትና ማንነት የማይወክል ስለሆነ ግፍ መፈጸም ከለመዱት ኣቢስኒያ ፋሽስቶች ጎን የማይቆምና ከማውገዝ ባሻገር እንደምታገላቸው የሲዳማ ብሄራዊ ነጻነት ግንባር ያስታውቃል።

4ኛ/ የኣዋሳ ዩንቭርስቲ ፕረዝደንት ኣቶ ኣያነው(ኣያኖ)በራሶ በኣስቸኳይ ከስልጣኑ እንድወርድና ያወጣውን ገንዘብ እንድከፍል በህግ እንድጠየቅ-ካለው ንብረቱ ተሽጦ እንድከፈል፡

5ኛ/ ደስታ ሌዳሞ፡ ኣለማየሁ ጥሞትዎስ፥ ጸጋዬ ቱኬና ኣብርሃም ማርሻሎ የዘረፉትንና ያባከኑትን የህዝብ ሀብትና ገንዘብ ወደ ካዝናው እንድመልሱና ስልጣኑን የሲዳማ ምክር ቤት ለምሰይማቸው እንድያስረክብ። ገንዘቡን መክፈል ካልቻሉ ያለው ንብረታቸው በእነሱም ሆነ በቤተስባቸው የተመዘገበ ተሽጦ እንድከፈል።

6ኛ/የሲዳማን ህዝብ ደህንነት ኣደጋ ላይ የጣሉት ግብዝና እውቀተቢሶቹ እነደስታ ሌዳሞ፡ ኣለማየሁ ጥሞትዎስ፥ ኣብርሃም ማርሻሎና ጸጋዬ ቱኬ መሆናቸውን ህዝቡ ኣውቆ በኣማራ ርስት ኣስመላሽ ጦርነት ተመልምለውና ተገደው ለምያልቁት የሲዳማ ወጣቶች የምጠየቁ መሆናቸውን ታውቆ የሲዳማ ህዝብ ጸረ-ህዝብ ና ጸረ-ዲሞክራስ ለሆነው ወታደራዊ ምልመላ ልጆቻችሁን ኣንዳትሰጡ ግንባሩ ጥሪ ያቀርባል።


የመብት ጥሰት በሲዳማ የምቆመው ኣሳሪዎችንንና ኣስገዳዮችን ስናስወግድና ስልጣንን የህዝብ ስናደርግ ብቻ ነው፡፡

ድል ለህብረብሄር ፈደራሊስት ሀይሎች

እናሸንፋለን