Sidama Liberation Front

header hb

ከሲዳማ ብሄራዊ ነጻነት ግንባር በወቅቱ ሲዳማን በተመለከተ የተሰጠ መግለጫ

June 10/2023

በሲዳማ ሰሞኑን እንቁራሪቶች ለምን ይንጫጫሉ?

እለማችን በጦርነት፥ በሽብርተኞች ግድያ ፥በመፈንቅለ መንግስት እና በተፈጥሮ ማለትም በድርቅ  እንድሁም በረሀብ መከራዋን ኣይታለች፤ እያየችም ነው ። ኢትዮጵያ ይህ ሁሉ በተደጋጋም ደርሶባታል። ግን ይኽ የሆነው ኣንዴም በህዝቡ ስንፍና ወይም ንቃተ ሂሊና ማነስ  በይበልጥ ግን ከእውቀተቢስ መሪዎች ምክንያት ነበረ፥ ኣሁንም ቀጥሎኣል። ኣስደንጋጩ ጉዳይ አሁን ያለው የ7ኛው ንጉስ መንግስት ህዝብን ኣራቁተው ሀብትን በጥቅቶች ዘንድ እንድከማች በማድረግ ብልጽግና እያሉ በድፍረት በኣደባባይ ይናገራሉ። ህዝቡን በተለይ ወጣቱን በሀስተኛ ነቢያት ስብከት በማደንቆር የስራ ኣጥነት ጥያቄ እንዳያነሳ ተደርጏል። ህዝቡ ደግሞ ልብን በምመስጡ ንግግሮችና ተስፋዎች እንድጃጃል ተደርጏል። የዚህ ሰለባ ከሆኑት ክልሎች ግንባር ቀደሙ  ሲዳማ  ነው።  የሲዳማ ህዝብ ሌሎች ህዝቦችን በማንነታቸው አይጠላም፤ የምጠላው ማንነታንን የማይቀበሉትን ነው።  ለስንት ዘመን ከፋፍለው ገዙን? ለስንት ዘመን እየገደሉን ማንነታችንን ክደው ዛሬም  ጭምር ይሳለቁብናል። እነሱ ተምረው ሃብታችንን ዘርፈው ከብረው ኣሁንም ኣዋርደው ልገዙን በኛው ገንዘብ ልጆቻችንን ገዝተው ይከፋፍሉናል። በየግዜው እየተቀያየሩ ይሾሙብናል ከዝያም ይገደሉናል። ሲዳማን ያልገደል ማን ኣለ?  ኣሁንም እሥራት ግረፋት ግድያ በሲዳማ ላይ ቀጥሎኣል። እስክ መቼ ሞትን ተሸክመን ለትውልድ ስናስተላልፍ እንኖራለን? እንዴት ነጻነት በገንዘብ ይሸጣል ወገኖቼ? እንዴት እነዝህ ሩቁ የማይታያቸው ትንሽ ጭንቅላቶ ይሳለቁብናል? ለእውነት የቆማችሁ ይህንን የአሀዳውያንን  ሴራ ከኣወቃችሁ ወደህዝባችን ተመለሱና ይህንን ደባ እየተሰራበት ያለውን  ህዝብ ንገሩት። የክልልህን  ሉዐላዊነትን መብትህንና ድምጽህ  ተቀምተሃል በሉት።ዛሬም አንተ የሥልጣኑ ባለቤትነትህን ቀምተው ምስሌኔ ይሾሙብሀል። እነዝህ እግራቸው የተቆረጠባቸው ባዶዎች እንዴት የ 7 ሚልዮን ህዝብ ድምጽ ይቀማሉ..  የምገርመው ነገር ቢኖር ሲዳማ ህዝብ የታገለው ራሱን ለማጥፋት ኣይደለም።የታገልነው በውርጋጦች ለመሰደብ ኣይደለም። የታገልነው ለድህነትና ዘራፍዎችን ለማንግስ ኣይደለም።የታገልነው ጥገኛ ለመሆንም ኣይደለም። የታገልነው የሌላው ግሳንግስ ባህል ተሸካም ለመሆን ኣይደለም። መሬታችንን ሸጠን ህዝባችንን ነቅለን ሌላውን ለመትከል ኣይደለም።  የታገልነው ነጻና ኩሩ ህዝብ ሆነን ትውልድን ለማሻገር ና ለማስቀጠል ነበረ።ዛሬ ሲዳማ የገጠመው ፈተን ከቀድሞ ስርኣቶች የባስ ነው።ይህ የኣሁኑ ጠቅላይ ሚንስትር ተብየው ወደ ስልጣን ከመጣ 4 ኣመት የሰራው ነገር ቢኖር መጥፎ ስራቸውን የምያጋልጡ  ተቃዋሚ ፓቲዎችን በማጥፋትና ተቃዋሚዎችን በመግደል ነበረ። የዘር ፍጅት በኦሮሞ፤ ትግራይ ሱማሌ፡ ሲዳማ”፡ ቤናሻንጉል፡ ቅማንትና አገው ህዝብ ላይ ከአማራ ነፍጠኞች ጋር በመሆን ፈXሞአል። የዝህ ዋና ኣላም የምተነፍስ እንዳይኖር ዘራፍዎችን እንዳይጋለጡ የእሱና የቦቹ ተግባር ለመሸፍን ኣምባገነናዊ አሀዳዊ ስርኣት በመትከል ነበረ።በዚህ ሂደት የሲዳማ ኣርነትን መሪዎችን በገንዘንብ በመገዛት የማክሰም ሰራ ሰርቶኣል። ይህ ተግባር  መጀመሪያ ያለተቃዋሚ ገመንግስቱን ቀዶ ለመጣል ከነፍጠኖች ጋር በኦሮማራ ህብረት የተዋዋሉትን ተግባራዊ ለማድረግ ነበረ። የለውጡ ጎርፍ ቆሻሻውን ይጠርጋል ቢባል ቆሻሻውን ኣምጥቶ ኣራግፎብን ሄደ። የዲሞክራሲ ምኞት ተቀበረ፡ የተሰጠን ቢኖር የሙታን መቃብር ቆጣር ብቻ ሆነ። ልጆቻችንን በልቶ የምጨርስ ኣውሬ መጣብን። የጠገቡ ካዲሬዎችና ኣሽከሮቻቸው በየሚድያው ኣቀረሹብን።  ኣንድ ኣባባል ኣለ “ እንቁራሪቶች ሀይቅ ዳር ቢንጫጩ ሀይቁ የነሱ መስሎኣቸው ይሆናል ግን እውነቱ ይህ ኣይደለም።  ሲዳማ ክልል የእንዝህ እንቁሪራቶች ሳትሆን 7 ሚልዮ ምርጥ ዜጎች መኖሪያ ናት። የአሁኑ የሲዳማ ፖለቲካ ና እኮኖሚ ነቀርሳዎች ደስታ ሌዳሞ የሚመራው ቡድን ነው።  ይህ ቡድን ትናንት በፕላንግ ኮሚሽን ሥር ያለ የብልXግና ፖሊስ እንስትዩት አደረኩ ያለ መሰረተቢስ ጥናት ተባባርና ሲዳማ ክልል መሆነና  ስሙን  አይፈልግም ይፍረሰልን ብሎአል ያሰኘ የከሀድዎች ስብስብ ነው።

የሲዳማ ህዝብ ሆይ

አሁን በአማራ ክልል የሚደረገው ጦርነት የአማራ አክራር ሀይሎች ትናንት አቢይን አካልበው ትግራይ ላይ የህዝብና የንብረት ውድመት ጦርነት ያሳወጁ፡ የኦሮሞን ህዝብ እስከዛሬ እያስገደሉና እያስፈXሙ  ይሉ ፋሽስቶች ናቸው። እነዝህ ህይሎች ትግራይን ከጨፈለቁ በኋል አቢይን አስወግደው ሥልጣን ላይ መቆናጠጥ ነው ብለው የተነሱ ሀይሎች ናቸው። ከአቢይ ጋር በህገመንግስት ማፍረስ ላይ ሁለቱም አንድ ናቸው፣። አቢይንና የአማራ አክራሪዎችን ያጣላቸው ከትግራይ በኋላ ሥልጣን የኛ ነው ብለው መነሳት ካል ሆነ በስተቀር ሁለቱም የዲሞክራሲ የህዝቦች ነXነትና የህብረ ብሄር ፈደራሊዝም ጠላቶች ናቸው። ለዝህ ማሳያው የሲዳማን ክልል ለማፍረስ የሄዱበት ርቀትና እየሰሩ ያሉት ደባ ግልX ማስረጃ ነው።

የሲዳማ ህዝብ ሆይ

  ልጆችህን የበላውን ፋሽስቱ  አቢይን የምያውቅ 83%  የኢትዮጵያ ህዝብ አለ። አቢይንና ብልXግናን ለፍርድ ለማቅረብ የምደረገው ትግል  ጊዜ የምሰጥ ጉዳይ አይደለም። በዝህም ከህብረ ብሄር ፈደራሊስት ሀይሎች ጋር የምደረገው የጋራ እንቅስቃሴ አሁን ከአልበት በአጭር ግዜ ማደግ አለበት ።  ታሪክ ብቻ ሳይሆን ህዝብ ይፈርዳል።  በከሀድዎችን መቃብር ብሩህ ህይወት ለመጪው ሆነ ለዛሬ ትውልድ የምሆን አገር ገነባል።አንጠራጠርም። የበሰበሰው ብልጽግና ኣይናቸው እያየ ይናዳል። ሲዳማም የርስቱ ባለቤት ይሆናል፡ዛሬ የሲዳማ ጠላቶች መሬቱን የምዘርፉ የብልጽግና ሌቦች ከሌላ ክልል ዘርፈው ኣዋሳ የመሸጉ፥ በሀይማኖት ስም መሬት የገበሬውን የቀሙ፥ በኢንቭስትመንት ስም መሬት ወስደ የሸጡና የገዙ  የግዜ ጉዳይ እንጂ ሁሉም ለባለቤቱ ይሆናል,። ከሁሉ ይበልጥ ሲዳማ ማወቅ ያለበት አንኮታኮትከው ኦርቶአማራ ፋሽስቶችና ብልXግና ተደራጅተው መጥተዋል።በደምህ የXፍከውን ታሪክህን ልያፈርሱ አቢይ በምባል ተኩላ በጀርባህ እያሰሩብህ ይገኛሉ።   ከሴረኛው ኣሀዳዊ ሥርኣት በደማችን ፈልቅቀ ያስከበርነውን ክልልነት  ስደፈርና የዝንጀሮች መፈንጫ ስሆን ዝምታ የለም። አማራ ስለጠላ ህገመንግስት አይፈርሰም ፤ አይሸራረፍም።አማራ ጂኦግራፍያዊ ክልል ከአማረው ራሱን ክልል ይበትን። ስለሌላው መናገር መብት የለውም።አይችልምም።

  ድል ለህብረብሂር ፈደራልዝም