Sidama Liberation Front

header hb
6ኛው ምርጫ ተብየው ክልሎችን ለማፍረስ የሚደረግ የኣሀዳውያን ሴራ ነው
 

ከሲዳማ ነጻነት ግንባር የተሰጠ መግለጫ

ጁን 16 2021

ኢትዮጵያ የምትባል ኣገር  ከቀድሞው ኣቢስንያና ኋላም በምንልክ ወረራ የተጠቃለሉ ከኦሮሚያ እስከሲዳማ፥ ከኣፋር እስከ ኦጋደን፥ 45ቱ የደቡብ ብሄርብሄረስቦችናከጋቤላ እስከቤናሻንጉል ይሉትን ህዝቦች  ጨፍልቆ በሀይል የተመሰረተ ነበረ።ምንልክ በወቅቱ በነበረው የመሳሪያ በላይነት የተወረሩ ህዝቦችን ማንነት ለማጥፋትና የወራረው ባህል እንድቀበሉ የተደረገው ሙከራ ሙሉ በሙሉ  ከሽፎኣል። ይህንን በመቃወም የተጀመረው ትግል የደርግን ስርኣት በማፈራረስ  በተለየም በ1991  መጨረሻ ተደረገው ስምምነት መሰረት የተረቀቀው ህገመንግስት ኣገርቱን ከመበተን ኣድኖ እንደ ኣገር ለማቆየት ኣመቺ ሁኔታ ፈጥሮ ነበረ። ይህም ብሄር ብሄርሰቦችና ህዝቦች በእኩልነት ተሳስበውና ተቻችለው የመኖር እሳቤ የያዘ ሰነድ ነበረ።ህገመንግስቱ ስጸድቅ 9 ክልሎች ተመስርተው ነበር። በቅርብም ሲዳማ ረፈሬንደም  በማካሄድ 10ኛው ክልል ሲሆን  ከኣስሩ ክልሎች ኣንዱ የሆነው የኣማራ ክልል  የቀድመውን ኣሀዳዊ ስርኣት ለመመለስ  ጫፍ የደረሰበትና ሌሎች ህዝቦች መብትና የእኩልነት ጥያቄን በዘር ፈርጆ በጠቅላይ ሚንስትር ኣብይ መሪነት ህገመንግስቱን ለመናድ እየተዘጋጀ ይገኛል። ። ኣገርቷ የተመሰረተችበት ሁኔታ እንዳለ ሆኖ ለዘመናት ያደፈውን ታሪክ በእውነተኛ የህዝቦች ታሪክ ለማስተካከልና የእንዝህ ህዝቦች ማንነት ታውቆና ተከብሮ ራስን በራስ የማስተዳደር መብት እውቅና በኣሁኑ ህገመንግስት ቢያገኝም በጨቁኝነት ተንሰራፍቶ የቆየው ቀኝ ሀይል ለኣገርቷ ዲሞክራሲያዊ ሂደት ደንቃራ በመሆን የህዝቦችን ደም በማፍሰስ ተጠምዶኣል።  ይህንን በህዝቦች ፍላጎት የጸደቀውን ሀገመንግስት ለመሻር በተነሱ በኣብይና ኢዜማ ጥምረት ደም ኣፋሳሽ ጦርነት በትግራይ ቤናሻንጉልና ኦሮሚያ እየተደረግ ይገኛል፥፡ ዛሬም ኢትዮጵያ እያልን የምንጠራት ኣገር የሬሳ ተሸካሚዎች፥ ሞትን የምሸጡ ነጋዴዎች ሱቅና   ህጻናትና ሽማግለዎች በቦንብ የምገደሉባትና  እናቶች የሚደፈሩባት ኣገር ሆና እያለች  ምን ኣይነት ዲሞክራሳዊ ምርጫ ይካሄዳል? ዘግናኝ ጨካኝነት የኣገርቷ መገለጫ በሆነባት ኢትዮጵያ  ኣሳፋሪዎች በሬሳ ላይ እየተረማመዱ ገዳይን ያጅባሉ፥ ምርጫም ብለው ይወሸክታሉ። ይህ ልታሰብ የሚገባ ኣይደለም። ግን ኣምባገነኖች በኣገር ኣንድነት ስም ጥቂት ምሁራንን በገንዘብ በመግዛት የተቀረውን በሀይል ኣንበርክከን እንገዛለን ባሉት መሰረት እያደረጉ ናቸው።

የሲዳማ ህዝብ ሆይ

በኢትዮጵያ ዲሞክራሲን የመረዳት ችግር መኖሩን ኣይተሀል። ለዚህም ዋናው ምክንያት የብዙሀን ፓርቲ ስርኣት ፍርሀት  መኖርና ቢኖርም የሚያስፈራቸው ሀይሎች መኖራቸው ነው.።ከዚህም በተነሳ ጉልበት ያለው ሁሉንም ኣጥፍቶ እኔ ብቻ ልኑር እሳቤ ስለኣለ ህዝቡ መብቱን ለማስከበር ኣልተቻለም።ዛሬ ኣሀዳዊ ሀይል ስልጣን ላይ ተመልሶ መጥቶኣል። የኣገርቷን የደህንነትና ወታደራዊ መዋቅር በመጠቀም ተቃዋሚዎችን  በማሰር፥ በመግደል ፥ እንድሰደዱ በማድረግ ፕርቲዎችን በመክሰስ፥ በሽብርተኝነት በመወንጀል ከሰላማዊ ትግል ሜዳ ገፍቶ በማስወጣት  ደም ኣፋሳሽ ጦርነት በኣገርቷ  እየተካሄደ ይገኛል። በተደረገው ሴራና ተንኮል  ብልጽግና ብቻ  ለምርጫ ራሱን ተፎካካር ኣድርጎ ኣቅርቦኣል።ይህንን ለመቋቋም ፓርላማው ሆነ የፍትህ ስርኣት ኣቅም የለውም። ፓርቲዎች የተቋቋሙበትን ኣላማ ለፍትህና ለብሄር በሄርሰቦችና ህዝቦች  መብት ጥያቄ መሆኑ እየታወቀ ጥቂቶችን በጥቅም በማንበርከክ ፓርቲዎች እንድፈርሱ ኣልያም የፋሽስት ፓርቲው ብልጽግና ተቀጥላ  እንድሆኑ ተደርገዋል።  በሲዳማ የሲኣን ኣመራሮችና በሀድያ በበየነ ጵጥሮስ የሚመራው ኢሶደፓ  በጥቅም ከተገዙትና ህዝቡን ከካዱት ጥሩ ምሳሌዎች ናቸው። ይህ የተደረገው በዲሞክራሲ እጦት ምክንያትና የዲሞክራሲ ጉዞ በኢትዮጵያ በመጨናገፉ ነው። ኣሁን የተያዘው የብልጽግና ጉዞ ምርጫ ኣካህጃለሁ በማለት ህገመንግስት ለማፍረስና የብሄር በሄረስቦችን የራስን እድል በራስ ለመወስን  የምደረገውን ጉዞ ለማደናቀፍ  የሚደረግ ሴራ ነው። ግን  ከንቱ ደም ለማፋሰስ ካልሆነ በስተቀር ህገመንግስቱን ማፍረስ ኣገርቷን እንደምያፈርስ  ነፍጠኛው ማወቅ ኣለበት።  ያኔ ተጎጅ ማን እንደሚሆን የምናየው ይሆናል።   እሁን ኢትዮጵያ  የምያስፈልጋት  ምርጫ ኣይደለም። ምርጫ የምያካህድ ህዝብ የተረጋጋ ሰላም ያለው ህዝብ ነው። በኢትዮጵያ ምርጫ ለማካሄድ ቀርቶ የህዝብ ምዝገባ እንኳ በኣግባቡ ማካሄድ ኣልተቻለም’  ስለሆነም  ለሲዳማ ህዝብ ግልጽ ለማድረግ የምንፈልገው  264 ልጆችህን ገድሎ የቀበረውንና የነፍጠኛ ተላላኪ  የሆነውን ብልጽግና ለመምረጥ መውጣት ክፋትን ላለማየት የተሰውትን  ወገኖችን ሬሳቸው ላይ መረማመድ መሆኑን ኣውቀህ ከገዳዮችህ ቄራ ምርጭ ርቀህ ስማእታትን በማስታወስ እቤትህ ኣንድትውል እናሳስባለን። ብልጽግናን መምረጥ ህብረብሄራዊ ፈደራሊዝምን ማፍረስ መሆኑን እንድታውቅ ኣስቀድመን እናሳስባለን።ይህንን ሲዳማ ህዝብ የሚቀበለው ስለኣይደለ ይህንን ገዳይ ፋሽስት መንግስት በመሳሪያ የታገዘ መሆኑን ኣውቀህ ተገቢውን ዝግጅት ማድረግ ቀዳሚ ተግባርህ ይሁን።  በተጨማርም የሲዳማ ነጻንት ግንባር የሚከተሉትን ውሳኔዎች ኣስተላልፎኣል።

  1. የውሸት ምርጫ ካርዶችን ሃዝቡ ማቃጠልና በእለቱ ወደምርጫ ጣቢይ ተብየው ከመሄድ ቤት እንድውል፤
  2. ኣሁን በስልጣን ላይ ያለው ፋሽስት መንግስት ኣገርቷን በውጭ ሀይሎች ኣስወርሮ ዜጎቹን በግፍ ያስገደል ከሀድ ሲሆን ዛሬ በትግራይ፥ ኦሮሚያና ቤናሻንጉል ወግኖቻችን ላይ የምፈጽመው ግፍ እንድቆም እንጠይቃለን።
  3. ያልተሸራረፈ የህዝቦች ራስን በራስ ማስተዳደር መብትለማስከበርና ለተግባርያዊነቱ ህብረፈደራሊስት ሀይሎች ጥምረት መፍጠር ተገቢ መሆኑን በመረዳት ለዝህ የቆሙ ሀይሎችና ፓርቲዎች የተቀናጀ ትግል እንድያደርጉ ጥሪያችንን እንቀርባለን።
  4. የኤርትራ ጦር በኣገሩ የሚበላውንና የሚጠጣው የሌለው በኣገኘው ኣጋጣም  ህዝባችንን በመግደልና ሴቶችን  በመድፈር በኣለም ሀያላን መንግስታት  ጭምር የተወገዘው በኣስቸዃይ ከትግራይና ከኦሮሚያ  እንድወጣ በምያመች ሁኔታ ሁሉ ድምጻችሁን  ማሰማት ኣለባችሁ።
  5. የኢትዮጵያ ችግሮች የሚፈቱት በህዝቦች የጋራ ምክክር ስለሆነ በኣገርቷ የታሰሩ የፖለቲካ እስረኞችን በመፍታት፥ በጫካ ያሉትን የቤናሻንጉል ነጻ ኣውጭ ፥ ህዋሀትና ኦነግን ጨምሮ ሁሉን ባለድርሻ ኣካላትን ያካተተ የሽግግር መንግስት ማቋቋም ኣስፈላጊ በመሆኑ ለዝህ ተግባራዊነት ኣጥብቀን እንሰራለን።

ድል ለህብረብሄር ፈደራሊስት ሀይሎች

ሞት ለቀኝ ሀይሎች

ጁን 16 2021