Sidama Liberation Front

header hb

ውርደትን ካባ ያደረገውና ውሸት የማይሰለቸው ነፍሰገዳይ የብልጽግና  ቡድን ሴራ በሲዳማ ክልል

September 2/2022

ከሲዳማ ብሄራዊ ነጻነት ግንባር የተሰጠ መግለጫ

ኢትዮጵያ የምትባል ኣገር ከተመሰረተችበት ዘመን ኣንስቶ በውስጧ በኣሉ በተለይም በደቡብ ህዝቦች  ላይ ግፍ በመፈጸም የሚትታወቅ ሲትሆን ተሿሚዎችም ይህንን ግፍ ባማስፈጸም የተካኑ እንድሆኑ የሰለጠኑ ስብእናቸውን የሸጡ  ሰው መሳይ ሙጃዎች ነበሩ። በተለይም ከ1993 ጀምሮ ለውጥ ተብየው የራሱ ልጆች ናቸው ተብለው በተሾሙ ስርኣቱን በማይመጥን ከነፍጠኛው በባሰ ጉዳት ኣድርሰዋል። እንዝህ በደም ሲዳማ ሆነው በተግባር የነፍጠኛው መርፌ ተውግተው የተኮላሹ የገንዘብና የጥቅም ባሮች ናቸው። 

ሰሞኑን በመገናኛ ብዙሀንና ሶሻል ሚድያ  የሲዳማ ነጻነት ሰራዊት (ሲነሰ) ተመሰረተ፥ ስልጥኖ ተመረቀ የሚሉ መግልጫዎችና ወታደራዊ ምልምሎች ምረቃ ከሲዳማ ብሄራዊ ነጻነት ግንባር ጋር በማያያዝ ስሰራጩ ተመልክተናል። የሲዳማ ብሄራዊ ነጻነት ግንባር ኣርማ በመጠቀም  የገንዘብ መዋጮ ጥያቄ (GO fund sidama national army)በማለት ኣሁንም የሲዳማ ብሄራዊ ነጻነት ኣርማ በመጠቀም ለመሰብሰብ ሞክረዋል። ይህ ሁሉ ድርጅታችንን የማይወክል መሆኑን ለግንባሩ ኣባላትና ደጋፍዎች እንድሁም ለሲዳማ ህዝብ ማሳወቅ እንወዳለን። ይህ የሲዳማ ነጻነት ሰራዊት የሚባለው በሲዳማ ክልል ኣመራር ነን ባዮች የኣቢይ ተሿሚ ከሀድዎች በደስታ ሌዳሞ፥ ኣብርሃም ማርሻሎ፥ ኣለማየሁ ጢሞትዎስ ና ታሪኩ ለማ የምመራ ሲሆን ኣላማውም በኦሮሚያ ኦነግ ሸኔ ና ኣባቶርቤ ብለው እነሽመልስ የኦሮሞን ህዝብ እንድምጨፈጭፉ ታሳብ ተደርጎ የሲዳማን ህዝብ በስውር ለመጨፍጨፍ የተመሰረት ነው።  እነዚህ በፍቶግራፍ ላይ የታዩት ወታደር ነን ባዮች ለዝህ ኣላማ የተመለመሉ ወንጀለኖች ሲሆኑ ወደፍት የምጠየቁ  ናቸው። ወንጀለኞች ኣይደለንም ካሉ ኣሁኑኑ ለህዝብ ቀርበው ማስተባበል  ኣለባቸው።  ይህ ካልሆነ ነገ በወንጀል ተባባሪነት ብቻ ሳይሆን በህዝብና በኣገር ክህደትና በነፍሰገዳይነት ይጠየቃሉ። የሲዳማ ብሄራዊ ነጻነት ግንባር ከዚህ ወንጀል ማስፈጸሚያ የነፍጠኛ ተንኮል ሰራዊት ጋር ምንም ግንኙነት እንደለለው ማሳወቅ እንፈልጋለን። የዝህ ሰራዊት ኣመሰራረት ዋናው ኣላማው በተገኘው መረጃ መሰረት የሲዳማ ፈደራሊስት ፓርቲ መመስረትና ፓርቲው ባገኘው የህዝብ ደጋፍ  ተደናግጠው የፈጠሩት ወንጀል ማስፈጸሚያ መሳሪያ ነው።የሲዳማ ህዝብ ብልጽግና ላይ እምነት ኣጥቶ ፍቱን ወደኣዲሱ ሲዳማ ፈደራሊስት ፓርቲ በማዞሩ ተስፋ የቆረጠው ብልጽግና ይህንን ድርጅት ለማጥፋት ታስቦ እየተሰራ ያለ መሆኑ መረጃ ኣግኝተናል። ይህ እኩይ ተግባር በኣቢሲንያ ኢምፓየር  በነፍጠኛው ተላላኪዎች ስፈጸም የቆየና መልኩን ቀይሮ የመጣ ታላቁ የፖለቲካ ሴራ ኣካል ነው። ህዝብ ገድሎ ፥ ኣስሮ የተሳካለት የለም። ከኣጼ ሀ/ስላሴ  ጀምሮ ኣሁን እየተንገዳገደ ካለው ኣቢይ መንግስት ድረስ ደም ኣፍሰው ኣልተሳካላቸውም። እየተፈጸሙ ያሉት ወንጀሎች ህዝብ ላይ ስለሆነ የተደበቁ ኣይደለምና ኣያመልጡም። የኣገርና የህዝብ መሪዎች ከራሳቸው በላይ ለህዝብ ኣሳቢ መሆን ስገባቸው  በገዛ ኣገራቸው ህዝብ ላይ ወንጀል መፈጸም የለየለት ክህደት በመሆኑ ቀድመው ማወቅ  ይገባቸው ነበረ።ዛሬ በኣገርቷ የምደረገው ሁሉ ስልጣን ላይ ያሉትን ጥቅም ለማስጠበቅ ህዝብ ላይ ወንጀል የምፈጸምበት ስለሆነ ይዋል ይደር እንጅ ከመጠየቅ ኣያድናቸውም።

በመጨረሻም ለሲዳማ ብልጽግና ለማሳወቅ የምንወደው በሲዳማ ህዝብ ላይና በህዝብ ወገኖች ላይ ወንጀል ፈጽማችሁ የምትገቡበት ቤታቸሁን እያፈረሳችሁና እየፈረሳችሁም  መሆኑን ኣውቃችሁ ከዝህ እኩይ ተግባራችሁ እንድትቆጠቡ በጥብቅ እናሳስባለን።

ድል ለህብረብሄር ፈደራሊስት ሀይሎች

ሞት ለኣሀዳዊውያንና ለግብረኣበሮቻቸው