Sidama Liberation Front

header hb
.

                             የነቀዙ ምሁራን መንግስትና ሲዳማ ላይ የተቃጣው የከሀድዎች ሴራ 

                                  ከሲዳማ ብሄራዊ ነጻነት ግንባር የተሰጠ መግለጫ

ይድረስ  ለኣሮረሳ፥ ለጭሪ፥ለበንሳ፥ ለኣርቤጎና ለቦርቻ፥ ለሀገረሰላም፥ለመልጋ ወረዳ ህዝብና የሲዳማ ኣርነት ንቅናቄ ኣባላትና ደጋፍዎች በያላችሁበት፥

እንድሁም የዛሬውን እውነታ ተረድተው በመታገል ላይ ያለሄው ኤጀቶ  ትውልድ  በሙሉ

ብልጽግና የተባለ ኣውሬ ኩሩ ታሪካችንን ለመደለዝና  ለማጥፋት የሲኣንን ኣመራር በጥቅማ  ጥቅም በመግዛት ጎጆኣችንን ለማፍረስ ተነስተዋል። የሴራው ኣላማ ሀዳዊውን ስርኣት ምስረታ ለማቀላጠፍ በዜዴ የብሄር ድርጅቶችን ማፍረስ የኣብይ ግንባር ቀደም  ኣላማ ሲሆን ይኽውም የእነዝህ የብሄር ደርጅቶች መሪዎችን  በመደለያ መግዛት ካልሆነም እንደኦነግና ህዋሀት በሀይል መደፍጠጥን ግቡ  ኣድርጎ የተነሳ ሀይል ነው ። ይህም በሲዳማ በሲኣን ኣርማ ሥር ተሰባሰበው ደርግን፥ ኢሕኣዲግንና ኋላም ብልጽግናን ያንቀጠቀጠው ትውልድ ታሪክ ለመቅበር የታለመ ነው።የሲኣን ኣመራር ተብየው ታሪክ ያደሳሉ የተባለው የንዋይ ባርያ በመሆን የተዋጋነውን ኣላማ ረስተን የትናንቱን የነፍጠኛውን  ኣሀዳዊ ስርኣት በጓሮ በር ልያስገባብን እየተሯሯጠ ይገኛል። ይህንን የሚያስተምሩ በባንዳነት የተካኑ ኣብይና የነፍጠኛው ርዝራዦች ኣስተሳሰብ የተበከሉ በሲኣን ኣመራር ውስጥ  ሰርገው ገብተዋል። ሲኣን የሲዳማ መሪ ድርጀት እንጂ የነፍጠኛ ሥርኣት ኣስመላሽ የቀልባሾች መሳሪያ ኣይደለም።  የዚህ ክህደት መሪ  ዱካለ ላሚሶ የተባለው በኣብይ ዘመን ክልል ስለሆንን ኣብይን እደግፋለሁ ብሎ የሲዳማ ታጋዮችን ህይወታቸውን የሰውለትን ኣላማ ክዶ 156 ወንድሞቻችንና እህቶቻችንን ገዳይ ጎን ቆሞኣል። በዝህ ጉዳይ ተጠያቂ ዱካለ ብቻ ሳይሆን 15ቱም የስራ ኣስፈጻሚ ኮሚቴ ኣባላት ጭምር ነው።ስራ ኣስፈጻሚ ኮሚቴው  የነፍጠኛው ተላላኪ መሆን መብቱ ነው  ግን  የድርጅቱን  ኣላማ ለኣሀዳዊ ስርኣት መሸጥ ኣይችሉም። ኣዎን ህዝብ ስለመብቱና ነጻነቱ ስጠይቅ ኣምባገነኖች ሰላም ያጣሉ፡ ያኔ እንደ ሲኣን ስራ ኣስፍጻሚ ያሉትን ከሀዲዎችን ገዝቶ የህዝብን መብት ማፈን ዋና ተግባሩ ያደርጋል።በመሆኑም  የኣሁኑ የሲኣን ኣመራር የተነሳንለትን ኣላማና ጉዞኣችንን ለማሰናከል ቆሟል።

 "ኢትዮጵያ ኣገረ ሞኝ ነሽ ተላላ

የቆመልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ"  ብሎኣል ንጉስ ሀይለሥላሴ ኣርበኞቹን ኣሥሮ ባንዳዎቹን በመሾሙ የተበሳጨው ኣዝማሪ። ዛሬ በሲዳማን የሆነው ይኽው ነው። የሲዳማ ብልጽግና የሆዳሞችና የባንዳ ስብስብ ሲሆን የራሱ ርእዮተኣለም  የሌለው የኒኦ-ነፍጠኛ ተላላኪ-ጉዳይ ኣስፈጻሚ ነው። እነዝህም ከጅምሩ የሲዳማን ክልል ጥያቄ ለማኮላሸት ከሙፍሪያት ጋር ስሰሩ የነበሩ ናቸው።ታድያ የሲኣን ተልእኮ በምን ከብልጽግና ጋር ይገናኛል? የሲኣን ኣላማና ግብ በፕሮግራሙ መግቢያ ላይ በግልጽ የተጻፈው፥ 

1.የሲዳማ ብሄር የራስን እድል በራስ መወሰን መብት ህጋዊና መሰረታዊ የሰው ልጅ መብት መሆኑን፥ ይህም በተባበሩት መንግስታት ቻርተር ላይ በግልጽ የሰፈረውን መብት የተቀበለና  ይህንን ተግባራዊ ለማድረግ የሲዳማ ህዝብ የዲሞክራሲ መስፈን ወሳኝ መሆኑን በመገንዝብ የምታገል ድርጅት ሲሆን፥

2.  የሲዳማ ህዝብ ከማን ጋር እንደምኖር፥ የጋራ መንግስት ምስረታ በውዴታና በፈቃደኝነት ላይ የተመሰረት መሆን እንዳለበትና ምን ኣይነት ኣገራዊ ህብረት መኖር እንዳለበት  በሚደረጉ ውይይቶች ላይ ነጻና ሁሉንም የህብረቱ ኣባላት በምጠቅም መልክ መሆን እንዳለብት  በግልጽ ኣስቀምጦ የምታገል ድርጅት ነው።

ይህ ከላይ የተጠቀሰው ተግባራዊ የሚሆነው በቀዳሚነት በህዝቤ ውሳኔ የራሱ ክልል መመስረት፥ ከዚያም ግልጽና ነጻ ምርጫ ተካህዶ መሪዎቹን መርጦ፥ የሲዳማ ተወካዮች ምክር ቤት መመስረትናመሪዎቹን በግልጽና በነጻ ምርጫ መሰየም ነው። ይህም ስልጣን የህዝብ ከፍተኛው ኣካልና የስልጣኑ  የዲሞክራሲያዊነት ማራጋገጫ ነው። ኣሁን ያለው የሲኣን ኣመራር የሲኣንን ኣላማዎችንና ግቦችን ያላገናዘቡ ከተሜ ጭልፍት ምሁራን ናቸው።  ቭክተር ሁጎ የተባለ የፈረንሳይ ደራሲና ጸሀፍ ስለከሀድ መሪዎች እንድህ ብሎ ነበረ

‘The man who fights his own people is never a hero”። የራሱን ህዝብ ክዶ የቆመ በጀግና ጎራ በምንም መስፈርት ኣይታይም ‘ ይላል። የዛሬው የሲኣን ኣመራሮች

1ኛ/ የህዝቡን ጥያቄ በማራመድ ፈንታ የገዥውን ኣሀዳዊ ፓርቲ ጉዳይ ኣስፈጻሚ በመሆን የህዝባችንን ታሪክ ለመቅበር የተነሱ

2ኛ/የሲዳማን ህዝብ ፍላጎት ከሚጎዳ ለድህነት ከዳረገው ፓርቲ ጋር በመሆን የሲዳማን ህዝብ ከጎዱ መሬት ዘራፍዎች፥ የህዝብ ንብረት ሰርቆት ከፍጸሙ ጋር ተውዳጅተው የዝህ ሙስና ተካፋይ ሆኖኣል።

 3ኛ/ለሲዳማ ክልል ጥያቄ ስታገሉ የነበሩ 330 የሚሆኑ ወጣቶች ዛሬም በእስር እየማቀቁ ይገኛሉ። የሲኣን ኣመራር እነዝህን ለማስፈታት ያደረገ ምን ጥረት ኣልነበረም። ይህም የሚያሳየው በሰርጎ ገብነት ኣሀዳዊነት ከሚያራምዱ ጎን በመሰለፉ የኣፈናው ተባባሪ ስለመሆነ በቂ ማስረጃ ነው።

4ኛ/ የሲዳማን ህዝብን መርቶ ራስ በራስ ማስተዳደር መርህ በማታገልና ለኣላማዎቹ መሳካት ህዝቡን በብቃት ኣደራጅቶ የፖለቲካው ስልጣን ባለቤት  እንድሆን በማድረግ ፋንታ ህዝቡን በዳይ ለሆነ የትናንቱ ኣስተሳሰብ ኣራማጅ ለሆነው ብልጽግና  ኣጃቸውን ስጥተው በዝህ ፓርቲ ስም ተወዳድረዋል።ይህም የተደረገው በገንዘብ፥ በመሬት ስጦታና በስልጣን ድለላ ነው። ይህ ወራዳ ተግባር ታሪክ የማይረሳው ክህደት ነው።

5ኛ/እንዝህ የሲኣን ኣመራሮች ነን ያሉት የሲዳማን ህዝብ ብቻ ኣይደለም የካዱት በጋራ ለመታገል  የተስማሙትን ህብረ ብሄር ፈደራሊስት ሀይሎች ኣባል የሆነውን መድረክን ጭምር የካደ ነው።

ስለሆነም የዛሬው የሲኣን ኣመራር ተብዬው የህዝቡን ፖለቲካ  ኣላማዎችና ግቦችን እንደዘመኑ ሸቀጥ ኣድርጎ ለእኔ ከተመቸኝ በማለት ሸጦታል።ለማንም ግልጽ መሆን ያለበት በዛሬይቱ ኢትዮጵያ ሀይማኖትና ፖለቲካ ሸቀጥ ሆነዋል።ሰዎች ለማያምኑት ሁሉ ለንዋይ ሂሊናቸውን ይሸጣሉ።ገዥው ከፈለገ ጥሩ ክፍያ በመስጠት ይገዛቸዋል።በዝህም ግብረገብነት ቦታ እያጣ የግለስብ ፍላጎት ሟሟያ መሳሪያ ሆኖ ያገለግላል። ኣብያተክርስትያናት ግብረገብነት የጎደላቸውን  እንደሽርሙጥና ድቃላ መውለድ፥ ፍቺ፥ግብረገብነት የጎደላቸው ጉቦኝነት፥የህዝብ ሀብት ሰርቆትና ዘራፍነት፥ በገንዘብ በተገዙ የምፈጸሙ ተራና የፖለቲካ ወንጀሎችና ግድያዎች ና ስያውግዙና ስያስተምሩ ኣይሰሙም።ይህ የሚያሳው የኣምነት መሪዎች ንዋይ ከመፈለግ ኣኳያ ይህንን ማንሳት የምጎዳቸው በመሆኑ ገብረገብነት ቦታ ኣጥቶኣል፥በዚህም ውሸት ነግሶኣል።   መሪዎችም  ህዝብ ይመራሉ ተብለው ሀላፍነት የተሰጣቸው የህዝብ ገንዘብ ከመስረቅ ባሻገር የፖለቲካ ደባ መፈጸም የተለመደ ጥሩ ባህል ኣድርገው ያዩታል።ስሾም ያልበላ ስሻር ይቆጨዋል የምሉት የፈውዳሉንና የዘራፍዎች ኣስነዋር ባህል፡በበጎነት ወደምታይት ከደረስን ሰንብተናል። ዛሬ በኣገራችን  “ምሁር” ተብየው የልማት መሪ በመሆን ፋንታ የህዝብ ንብረት በመዝረፍና በማዘርፍ የህዝብ ጠላትነቱን ኣስመስክሮኣል። ምሁራን ተብየዎች  ቢሮክራሲው ውስጥ ተስግስጎ የኣምባገነኖች መሳሪያ በመሆን በየዳሱና በየስብሰባው እየተገኘ ኣምባገነን መሪዎች በማሞገስ ለስላጣን ኣጎብዳጅ በመሆን ወጣቱን በጦርነት እየማገደ ይህንን እልቅት በበጎነት ይሰብካሉ፡፡ ይህም ፖለቲካውን በማቀጨጭ ህዝቡንና ኣገርቷን ኣደጋ ላይ የጣለና ምሁር ልማትና ኣዳዲስ ግኝቶች ፈጣሪ በመሆን ፈንታ ህዝብ የከፈለውን ግብርና የልማት ባጀት እየበላ ኣገርቷን የድህነት ሜዳ ኣድርጏታል።የመንግስት መ/ቤቶችም እነዝህን ቀፎ ምሁራን በመቀለብ ወደበጏ ኣድራጎት ድርጅት ተሸጋግረዋል።እነዝህ ሌላው የሰራውን የምበሉ ደካማ ምሁራን በፖለቲካው ግንባር ቀደም በሆኑበት እንደኢትዮጵያ ባሉት ድሀ ኣገሮች ዲሞክራሲ በኣምባገነንነት ተተክቶኣል ።  በሲዳማ ሆነ በኣጠቃላይ የኢትዮጵያ ፖለቲካ የገጠመው ችግር ይህ ነው፡፡

 በመሆኑም በዚህ ኣይነት የኣገርቷ ህዝብ በኣፋኞች እጅ መቀጠል የለበትም።ኣሀዳዊው ስርኣት በዲሞክራሲያዊ ምርጫ እንደሚሸነፉ ስለኣወቁ ፈደራሊስት  ሀይሎችን በማሰር፥ በመግደል፥በጉቦ በማኮላሸት ይህንን ማድረግ ባቃታቸው ቦታ ጦርነት በማወጅ በህዝብ ላይ ግፍ እየፈጸሙ ይገኛል። ይህንን የህዝቦችን መብትና ነጻነት ገፋፍ የሆውን የኣብይ መንግስት ማስወገድ ግዜ የምሰጠው ጉዳይ ኣይደለም። የሲኣንን ኣላማና የትግላችንን ግብ የካዱ ኣመራሮችና የኒኦ-ነፍጠኛ ተላላኪ ብልጽግና  መደምሰስ ያለባቸው መሆኑ የሲዳማ ህዝብ ኣውቆ  ለመብቱ ዘብ ይቁም። የሲዳማ ህዝብ በትግራይ ህዝብ ላይ በነፍጠኛው ሀይል የሚካሄደው ግድያ ተካፋይ መሆን ትልቅ ስህተት ስለሆነ ልጆቹን ወደጦር ሜዳ መላክ የለበትም።ሲዳማም 156 ልጆቹ የኣብይ ሰለባዎች ሆኖ ሳለ ያ መቼ ተረሳና ከገዳይ ጎን የምንቆመው? የሲዳማ ብልጽግና ሆነ የሲኣን አመራር የምጠየቁበት ግዜ ሩቅ ኣይደለም። ስለሆነም  ይህ ከሀድው የሲኣን ኣመራር ተብዬው ኣሁኑኑ ጠቅላላ ጉባኤ በመጥራት ምርጫ በማድረግ ስልጣኑን ለእውነተኛው ኣመራር ማስረከብ ኣለበት። ሲዳማ ህዝብ በኣገኘ ሁሉ ታጥቀህ  የራሳህን መብት ኣስከብር። ያለታጠቀ ህዝብ ራሱን ለባሪነት ኣሳልፎ የሰጠ መሆኑን ኣውቀህ በንቃት ቁም።ገዳይ ካልተወገደ ነጻነት ኣይኖርምና። 

ድል ለህብረብሄር ፈደራሊስት ሀይሎች 

 ሲኣን የሲዳማ ህዝብ ማህተም ነው።