Sidama Liberation Front

header hb

የቢድሶ ቦሮጄ ኮሌ /ኣየለ/ ኣጭር የህይዎት ማስታዎሻ

ቢድሶ ቦሮጄ ኮሌ በቀድሞው ሲዳማ ጠቅላይ ግዛት፣ ሲዳማ እውራጃ በሸበዲኖ ወረዳ ዲራሞ Dhanqo ቀበሌ ከኣባቱ ኣቶ ቦሮጄ ኮሌ ባንቁርሶና ከእናታቸው ስርብቱ ጠኣንሶ እኢኣ 1937 ተወለዱ። ከዝያም እድሜቸው ለትምህርት ስደርስም

ከ1ኛ - 4ኛ ክፍል ልእልት ተናኘ ወርቅ ሀ/ስላሴ ኣንድኛ ደረጃ ት/ቤት ለኩ ከተማ

ከ5ኛ -8ኛ ይርጋኣለም መካነየሱስ ት/ቤት

9=10ኛ ክፍል ራስ ደስታ ዳምጠው ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ይርጋለም

11ኛ ክፍል ሽመልስ ሀብቴ ሁለተኛ ደረጀ ት/ቤት ኣዲስ ኣበባ

12ኛ ክፍል ሀረር ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ሐረርጌ ተምሮኣል።

የኣቶ ቢድሶ ቦሮጄ Kole /ኣየለ/ የፖሊቲካና ማህበርዊ ህይወት

የቢድሶ ቦሮጄ ህይወት የምገለጸው ለህዝብ ባለው ታማኝነትና ከራሱ ጥቅም ይልቅ የህዝብን ጥቅም የምያስቀድም ስብእና ያለው ሰው መሆኑ ነው። ቢድሶ ጨቋኝ ና በህዝብ ላይ ግፍ የምፈጽም የፍውዳል ስርኣትን ያለርህራሄ የታገለ፥ የዝህ ስርኣት ፖሊሲዎች መፍረስና የብሄር ብሄርሰቦች መብት መከበር፥ ለፍትህ ለነጻነትና ለእኩልነት ግንባር ቀደም ታጋይ ነበረ። ቢድሶ በተለያዩ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ና ከሲዳማ ውጭ ለመሄድ የተገዶ ነበረ የዚህም ዋና ምክንያት ይ/ኣለም ሁለተኛ ት/ቤት ስማር የተማሪዎች ፕረዝደንት ሆኖ ስያገለገል ዘውድ ኣገዛዝን በመቃወም በምደረገው ትግል ተሳታፍ በመሆኑ በጸጥታ ሀይሎች ስለተፈለግ ኣካባቢውን ለቆ መሄድ ግድ ነበረ። ዋናው መንሴው የሆነው ኮሎኔል ይገዙ የተባለ የሲዳማ ፖሊስ ኣዣዥ ጋር የተማሪዎች መማክርት ፕረዚዳንት ሆኖ በምሰራበት ወቅት የተማሪዎችና የይርጋለም ከተማ ህዝብ ስብሰባ ተጠርቶ በተደረገ ስብሰባ ኮሎኔሉ ባደረጉት ንግግር በወቅቱ ተተማሪዎች በነበረው ቢድሶ ቦሮጄ ላይ የጥላቻ ናዳ ያወርዱበታል። ከንግግሩ “እንዴት እንድህ ኣይነት የሲዳማ እናት ትወልዳለች” ብሎ በንቀት ለተናገረው ቢድሶ የሰጠው መልስ ‘ኣዎን የሲዳማ እናት እንደተናገሩት ጀግና ወንድ ትወልዳለች ይልቁንስ ወንድ ኣርግዞ ማየት ነው እኔን የገረመኝ ” ብሎ መለሰለት። ኮሎኔ ይገዙ የታወቀ ጉበኛና ቦርጫም ነበረና ያንን በህዝብ ፍት በማጋለጡ በዝህ ንግግሩ የተበሳጩት ኮሎኔል ልያስይዙት ሞክረው ህዝቡን ከለላ ኣድርጎ ኣመለጣቸው።

ቢድሶ ጸረ ዘውደ ኣገዛዝ ትግል ውስጥ በሲዳማ ኣውራጃ ከፍተኛ ኣስተዋጽኦ ከኣደረጉ ና ግንባር ቀደም ታጋዮች ኣንዱ ነበረ። /ቢድሶ በምግባሩ ጭቆናን የማይቀበል የህዝብን በደል የራሱ ኣድርጎ የተቀብለ ሲሆን የህንን የወረሰው ብለን የምናምነው 

ከኣያቱ ነው ተብሎ ይነገርለታል።እያቱ ኮሌ ባንቁርሶ በሲዳማ ከምታወቁ ጸረ-ፍውዳልና ጸረነፍጠኛ ግንባር ቀደም ታጋዮች ክነበሩት ኣንዱ ሲሆን ድጃዝማች ባልቻ ኣባንፍሶን ኣዲስ ኣበባ ድረስ በመሄድ ኣቤቱታ በማቅረብ ሙሉ ሰብእና የሌለው ስለሆነ ሲዳማን ኣይገዛንም ቢለው በዝያን ጨለማ ዘመን የሞገቱ ናቸው። በዝህም ባልቻ ከሲዳማ እንድነሳ ተደርጏል፠። ቢድሶም የዝህ የጸረ ፈውዳል ግንባር ታጋይነት ከቤተሱቡ የወረሰ ነው.ብለን እናምናለን።

ቢድሶ ለፖለቲካ ነጻነት ከምያደርገው ትግል ጎን መሰረታዊ የኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ፍትህ ኣንድከበር መሬት ለኣራሹ መፍክር ኣንግቦ በግንባር ቀደምትነት ታግሎኣል፥፡ ቢድሶ የትምህርት ኣስፈላጊነት ቀድሞ የተረዳ ሲሆን በተወለደበት ገጠር ኣካባቢ ትምህርት ቤት ባለመኖሩ ህዝቡን በማስተባበር በወቅቱ የክ/ሀገሩ ትምህርት ቤቶች ስራኣስኪያጅ ከነበረው ኣቶ በለጠ ኣወቀ ጋር በመነጋገር በስዊድን ተራድኦ የትምህርት ቤቶች ህንጻ ስራ ድርጅት ኣማካይነት በሎካ ኣባይ ወረዳ የመጀመሪያ የሆነውን የጎርቤ ሳላ ኣንደኛ ትምህርት ቤት ኣስርተዋል።

ከሀይለስላሴ መውደቅ በኋላ ወታደራዊ ደርግ ስቋቋም እድገት በህብረት ዘመቻ ተሳታፍ በመሆን በቦረና ኣውራጃ በሀረቀሎ ዘመቻ ጣቢያ ዘመተ። የዘመቻው ዋና ኣላማ ህዝባዊ መንግስት ለማቋቋም ለምደረገው ኣመቺ ሁኔታ ይፈጥራል የምል ነበረ። ሆኖም ደርግ ይህንን በመጠቀም የራሱን ስልጣን ማደላደል በመጀመሩ ይህንን የምቃወም በወቅቱ ተደራጅቶ የነበረውን የፖለቲካ ድርጅት ኢህኣፓን ተቀላቅሎ ደርግ እንድወገድና ህዝባዊ መንግስት እንድቋቋም ትግሉን ቀጠለ። በዘመቻ ጣቢያ ትግሉ በጸጥታ ሀይሎች ክትትል መምራት ባለመቻሉ በተደረገው ውሳኔ ወደሶማሌ ለመሻገር ወስኖ ጉዞ ይጀምራል። በበረሀ በውሀ ጥማት ምክንያት ያንጀት መታጠፍ ስለኣጋጠመው በጉድኞቹ እርዳታ ይርጋለም ተመልሶ ታክሞ ድኖኣል። ከዚያም ተመልሶ መጀመሪያ በወላይታ ኣውራጃ ኦሞ ሸለቆ የትጥቅ ትግሉን ተቀላቀለ።ይህ ኣካባቢ ለትግሉ የማይመች በመሆኑ በድርጅቱ ትእዛዝ ወደኣዲስ ኣበባ ሄደው ከዝያም ወደትግራይ ኣስምባ ተጓዘ፡ በጎንደር ጫካ የኢህኣፓ ወታደራዊ ክንፍ ኣዛዥ በመሆን ተዋግቶኣል። በነበረው የውስጥ መከፋፈል ወታደራዊ ትግሉ ስዳከም በእግሩ ሱዳን ተጉዞ ከዝያም ወደ ኬንያ በመሻገር በተባበሩት መንግስታት ስደተኞች ኮሚሽን ኣማካይነት ወደኣሜሪካ ተጉዞ መኖርያውን ቴክሳስ ግዛት በማድረግ ኑሮዉን መሰረተ። ቢድሶ ኣሜሪካ ሆኖ የሲዳማን ኣርነት ንቅናቄ ከሶማሊያ ተነስቶ የሚዋጋውን የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ የረዳ ሲሆን ደርግ ውድቀትም በኋላ በሽግግሩም ወቅት በኣቶ ወልዳማኑኤል በኩል የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ የሲኣን ኣገር ቤት መዋቅር እንድዘረጋ ከፍተኛ ኣስተዋጾ ኣድርጏል። የኣቢይ ክህደት ሽግግር መንግስት ስመሰረት ለህዝባችን ብርሃን ይፈነጥቃል በማለት ከ40 ኣመት ስደት በኋላ ወደኣገር ቤት ተመልሰው ኣዋሳ ኑሮኣቸውን መስረተዋል።

ቢድሶ ቦሮጄ በ40 ኣመት ስደት ኑሮው ወቅት ወ/ሮ ማሪያ ፋሊስ ጋር ጋብቻ መስርተው የሶስት ወንድ ልጆች ኣባት ሲሆን በመጨርሻም በምኖሩበት በሲዳማ ክልል ዋና ከተማ ሀዋሳ በድንገተኛ ህመም ግንቦት 7 /2014ወለዱ 77 ኣመታቸው ከዚህ ኣለም በሞት ተለይተዋል.።

ታጋይ ይሞታል ትግለ ይቀጥላል!!

በዝህም ለቤተሰቡና ለትግል ጓዶቹ መጽናናትን እንመኛለን.