Sidama Liberation Front

header hb
.

በጠቅላይ ሚ/ር ዶ/ር አብይ አህመድ የሚመራዉ የኢትዮጵያ መንግስት ለሲዳማ ሕዝብ በአስቸኳይ መመለስ ያለበትን አንገብጋቢ ጥያቄወችን በተመለከተ ከሲዳማ ኤጀቶ የተሰጠ መግለጫ

የሲዳማ ህዝብ በታሪኩ ጭቆናን ኣሜን ብሎ ተቀብሎ የኖረበት ጊዜ የለም። ከኣፄዎቹ ጊዜ ኣንስቶ እስካሁኑ የኢህኣዴግ ዘመነ መንግስት ድረስ የተነጠቀዉን እራስን በራስ የማስተዳደርና ሌሎች ወሳኝ ደሞክራትክና ሰብዓዊ መብቶች ለማስመለስ ከፍተኛ ዋጋ ኢየከፈለ ቆይቷል። ለኣብነት ያክል ደርግን ለመጣል በተደረገ አልህ ኣስጨራሽ ትግል ብዙ ሺ የሲዳማ ጀግኖች ተሰዉተዉ ኣብዛኛዉን የሲዳማ ኣካባቢ ህወሃት ኣዲስ ኣበባ ሳይገባ ነፃ ማዉጣት ችለዋል።

በኢህአዴግ አገዛዝ ዘመንም ለነጻነቱና ህገ መንግሥቱ የሚሰጠው መብቶቹ እንድተገበሩለት እየጠየቀና ብዙ መስዋዕትም እየከፈለ ያለ ህዝብ ነው። ይሁን እንጅ የኢህአዴግ አገዛዝ ላለፉት ለ27 ዓመታት እራሱ ያዘጋጀውን ህገ መንግስት ከመተግበር ይልቅ የሲዳማን ሕዝብ ማፈንንና መጨቆንን መርጦ ሕዝቡ በራሱ መሬት ላይ የራሱን እድል በራሱ እንዳይወስን ህገመንግሥታዊ መብቱን ተንፍጎ ቆይቷል። ከዚህም በላይ የሲዳማ ህዝብ ጠንክሮ እንዳይወጣና የሚገባውንና የሚመጥነውን ቦታ አንዳያገኝ ብዘ ደባ ሲመታበት ቆይቷል። ለምሳሌ ያህል፤

፩. የዞኑና የክልል ምክር ቤቶች ያፀደቁትን ህገመንግስታዊ የክልል ጥያቄ ባለማስፈፀም የሲዳማን ህዝብ ልማትና ዕድገት ለ27 ኣመታት አንድጉኡተት ተደርጉኣል።

፪. ኢትዮጲያ ለዘመናት ለውጭ ምንዛሪ የምትተማንበት የቡና ምርት 40% የሚገኘው ሲዳማ ኣካባቢ ነው። በዚህም ምክናያት ብዙ ነጋዴዎች ጥሩ መንቀሳቀስ ሲጀምሩና ኣቅማቸዉ አየጎለበተ ሲመጣ TPLF ኣልተመቸዉም። ስለዚህ የሲዳማ ነጋዴውች ኣንዴ በደረቅ ቼክ ሌላ ጊዜ ብድር በመከልከል ክፉኛ ኢንዲመቱ ተደረገ። አስከ ዛሬ ድረስ ከጥቂት ነጋዴውች በስተቀር ብዙዎቹ በባንክ እዳ ተጠፍረው ይገኛሉ።

፫. በሃዋሳ ከተማና ኣካባቢ የሚኖሩ ገበሬዎች ያለ በቂ ካሳ አንድነሱና ለሎች በነሱ መረት አንድከብሩብት ኣይትደረገ ይገኛል።

፬. ለመብታቸው የሚታገሉ ዜጎች ታፍነዉ ይወሰዳሉ ይታሰራሉ ኣንዳንዴም ደብዛቸው ይጠፋል።

፭ በሙስና የህዝብ ሃብት ይዘረፋል፣ በዘመድ ኣዝማድ የተደራጁ የTPLF ኣሽከሮች ይቀራመቱታል።

፮ ተርቦ የማያዉቀዉ ሲዳማ፤ ዉሃ ስሉት ውተጥ የሚሰጥ ሲዳማ፤ ዛሬ ከረሃብ ጋር ስሙ ኣብሮ መነሳት ጀምሯል። እነዚህና ሌሎች ግፎች ያንገፈገፉት የሲዳማ ህዝብ ከሌሎች እትዮጵያዉያን ብሀረሰቦች ጋር በማበር ስርአቱን ለመቀየር በይበልጥ እየታገለ ይገኛል። ነገር ግን ክቡር ጠ/ም ኣብይ አህመድ ሲዳማን በሚጎበኙበት ኣጋጣሚ ከሲዳማ ህዝብ ጋር ለመታረቅ ባስቸኳይ መፈፀም ያለባቸዉን ጉዳዮች ማንሳትና ማስታወስ አንሻላን።

በአሁኑ ሰአት መንግስት በአስቸኳይ መመለስ ያለባቸው የሲዳማ ህዝብ አንገብጋቢ ጥያቄወች የሚከተሉት ናቸዉ፦

፩. በህገ መንግስቱ አንቀጽ 46(2) ላይ ክልሎች የሚዋቀሩት በህዝብ አሰፋፈር፣ ቋንቋ፣ ማንነት እና ፈቃድ የሚመሠረት ነው ብሎ ይደነግጋል። በዝህም መሠረት በኢትዮጵያ ካሉ ብሄረሰቦች በሕዝብ ቁጥር በ5ኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ የሲዳማ ሕዝብ የራሱ ክልል እንድኖረዉ ህገ ምንግስታዊ መስመር ተከትሎ በሲዳማ ዞን ምክር ቤትና በክልሉ ምክር ቤት በሙሉ ድምጽ ፀድቆ ዉሳኔ ሕዝብ መደረግ ስገባዉ እስካሁን ሳይተገበር ቆይቷል። ይህ ከሲዳማ ሕዝብ በቁጥር ለሚያንሱ እንኳን የተሰጠዉ ህጋዊ መብት ለሲዳማ ሕዝብ ተከልክሎ ደቡብ በምለዉ የአቅጣጫ ስያሜ እየተጠራ ብዙ ዋጋ እየከፈለ ቆይቷል ። ይህ አሰራር የሕዝባችንን ቁጥር፣ ማንነትና የጅኦግራፍ አሰፋፈርን ያላገናዘበና ይልቁን በትግራይ የበላይነት ለሚመራዉ የኢህአዴግ መንግስት ጥቅምና አሰራር ተብሎ ብቻ የተዋቀሬ በመሆኑ በአስቸኳይ የሲዳማ ህዝብ ጥያቄ መመለስና የሲዳማ ክልል ዕውን መሆን ኣለበት።

፪. ላለፉት 27 ዓመታት የሲዳማ ሕዝብ አንድም ቀን ያስተዳድረኛል ወይም ይመራኛል የሚለዉን አንድንም ሰዉ መርጦ አያዉቅም። በህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ በላይነት የሚመራዉ የኢህአዴግ መንግስት ግን ለግል ጥቅማቸዉ ያደሩትን ከሲዳማ ህዝብ ዉስጥ እየመለመ በፈለገዉ ጊዜና ቦታ እየመረጠና እያስቀመጠ ሕዝባችንን ስጨቁን ቆይቷል። እንድህ ያለ ኣሰራር በኣስቸኯይ እንዲቆምና የህዝብ ድምፅ እንዲሰማ እንጠይቃለን።

፫. የሃዋሳ ከተማ ማስፋፋት በሚል ሰበብ የተጀመረዉና በሺዎች የሚቆጠሩትን የሲዳማን አርሶ አደሮች የማፈናቀልና ለድህነት የመዳረግ አረመነያዊ ሴራና የተለመደዉ የመሬት ወረራ በአስቸኳይ መቆም አለበት። ፣በተለይም ከዚሁ አካባቢ ላለፉት 27 ዓመታት ለዘመናት ከኖሩበት ቀዬ እየተፈናቀሉ ለድህነትና ለጎዳና ኑሮ የተዳረጉ የሲዳማ አርሶ አደሮችና ቤተሰቦቻቸዉ በአስቸኳይ ካሳ ተከፍሏቸዉ እንድቋቋሙ እንድቋቋሙ መደረግ አለበት።

፬. በሃዋሳና በይርጋለም የተቋቋሙ እንዱስትሪያል ፓርኮች በሲዳማ መሬት ላይ የሲዳማን አርሶ አደሮች በገፍ በማፈናቀል በሕዝብ ጉልበትና ሃብት የተቋቋሙ በመሆናቸዉ ፓርኮቹ ወደ ህዝብ ሃብትነት ተሸጋግረዉ ለሕዝብ ጥቅም እንድዉሉ መደረግ አለባቸዉ፣ በገፍ የተፈናቀሉ አርሶ አደሮችም ሙሉ ካሳ ተከፍሎአቸዉ እንድቋቋሙ መደረግ አለበት።

፭. ተጠያቅነት ባጣዉ በኢህአዴግ መንግስት ብልሹ አገዛዝ የተነሳ በችግርና በድህነት ሥር የሚማቀቀዉን የሲዳማ አርሶ አደር በማዳበርያና በሌላ የስርቆት ሰበብ ማቆርቆዝና ጥቅት ሰብአዊነት የጎደቸዉን ኪስ ማሳበጥ መቆም አለበት።

፮. የሲዳማን ኣቅም የማዳከም ሴራና የሲዳማ ነጋዴዉች ላይ የተከፍተው ዘመቻ በፍጥነት መቆም ኣለብት።

፯. በተለያዩ ጊዜያት በሲዳማ ሕዝብ ላይ በደል የፈጸሙና ወንጀል የሰሩ የአገዛዙ አባላት ለፍርድ መቅረብ አለባቸዉበተለይም ግንቦት 16 ቀን 1994 ዓም በሎቄ በህገ መንግስቱ መሠረት በሰላማዊ መንገድ በደላቸዉን ለመግለጽ በወጡ ሰላማዊ የሲዳማ ህዝብ ላይ ጭፍጨፋ ያዘዙና የፈጸሙ ወንጀለኞች ለፍርድ መቅረብ አለባቸዉ።

እነዚህ ከላይ የተጠቀሱ አንገብጋብና ሌሎችም የሲዳማ ሕዝብ ጥያቄወች በአስቸኳይ የማይመለሱ ከሆኔ የሲዳማ ህዝብ ለብዙ ሽህ ዓመታት እራሱን መስዋእት እየከፈለ ያቆየዉን በአፈሩ ላይ እራሱን በራሱ የማስተዳደር መብቱን ለመማስመለስ የሲዳማ ኤጀቶ ከሲዳማ ህዝብ ጎን በመቆም የትዉልድ አደራዉን በብቃት ለመወጣት ትግሉን አጠናክሮ ይቀጥላል።

በሕዝብ ትብብር ጨቋኝና አረመኔያዊው ሥርዓት ይወገዳል! 
ኤጀቶ 
ሚያዝያ 15 ቀን 2010 
ሃዋሳ