Sidama Liberation Front

header hb

የዳንኤል ቢራሞ አጭር የህይወት

September 14/2023

ዳኔኤል ቢራሞ ከአባቱ አቶ ቢራሞ ሲአሞና ከእናቱ ከወይዘሮ ቃሮ ከታ ሚያዝያ 14/1944 አ/ም በደራራ ወረዳ ጩቃላ ቦረ ቀበለ ልዩ ስሙ ሞላተ ተወለደ። አባቱ ለትምህርት ባላቸው ጉጉት የተነሳ በአካባቢው ት/ቤት ስለሌለ ከሰፈሩ ርቆ ወንዶ ወረዳ ተወስዶ 1951-1954 አና 1956 አ/ም አለታ ወንዶ ስዊድሽ ኢንትርየር ሚሽን ከ1፟-4 ኛና 6ኛ ክፍል ተማረ። 1955 አ/ም አባታቸው ከብት ይዘው ሎካ አባያ ወደወላይታ አውራጃ ሲሄዱ አብሮ በመሄድ 1955 አ/ም 5ኛ ክፍል በሱዳን ኢንትሪር ሚስዮን ተማረ።ከ1957_1958 ማለትም 7ኛና 8ኛ ክፍል ይ/አለም መካነየሱስ ሚሽን ት/ቤት አጠናቆ በ1959፟ 1963 ትምህርቱን ይ/አለም ሁለተኛ ደረጃ ት/ ቤት አጠናቀቀ።

ዳንኤል 1966 አ/ም አዲስ አባባ በምገኘው ኮተቤ መምህራን ኮሌጅ ገባ። ዳንኤል የ60ዎቹ የXረ_ፍውዳል ትግልና የለውጥ ቀዳጂ ትውልድ ነበረና በመሀይምነትና ከዘመኑ ሥልጣኔ ተገሎ የነበረውን ህዝብ ለማስተማር በደርግ መንግስት በታወጀው የእድገት በህብረት ዘመቻ ተሳታፍ ሆኖ በሲዳማ ወንዶ ወረዳ ለሁለት አመት አገልግሎአል።ከዘመቻ መልስ ከኮተቤ መምህራን ኮለጂ በከሚስትር በዲፕሎማ ተመርቆ ኋላም ከአ/አ ዩንቨርሲቲ አሁንም በኬሚስትር በባችለርስ ዲግርተመርቆ ባሌ ጎባ በምገኘው ሁለተኛ ደርጃ ት/ቤት በኬምስትር መምህርነት ሰርቶአል።

ዳኔኤል 1967 አ/ም የመሬት አዋጂ ስታወጅ አዋጁን በሲዳምኛ ከተርጎሙትና በሬድዮ ለመጀምሪያ ግዜ አውጁን በሲዳምኛ ካሰሙን ሲዳማዎች አንዱ ነበረ።ቀጥሎም ሲዳምኛን በሳባውያን ቋንቋ ተXፎ በሲዳማ ውስጥ ለመሰረተ ትምህርት እንድውል ከጓደኞቹ ጋር አድርገዋል።

የደርግ ሥርአት ስገርሰስ የደቡብ ክልል በምለው በጠ/ሚንስትር ቢሮ ተመድቦ ሰርቶአል። ዳንኤል የሲዳማ መብትን በተመለከት የማይደራደር ህይወቱን በሙሉ የኖረበት አቋም ሲሆን ከጠ/ሚንስትሩ ቢሮ የለቀቀበት ዋናው ምክንያትም የደቡብ ክልል ጭፍለቃ በመቃወም ነበረ። ከሱ ጋር የነበሩት ለሆዳቸው ብለው እስከዛሬ ለህዝባችን መበደል ምክንያት የሆነውን አሀዳዊነትን ደግፈው እያጨበጨቡ ይገኛሉ።ዳንኤል በኢህአዲግ ቅጥረኞችና ለሆዳቸው በአደሩ ብዙ እንግለት ደርሶበታል። በዝህም ምክንያት በተለያዩ ግዜያት ስራውን ለቆ ኑሮውን ገጠር እንድሆንም አድርገውታል።

ዳን ኤል ከ1980 እስከ 1983 ድረስ ለኩ ሁለተኛ ደረጀ ት/ቤት ከዝያም 1982 ከ52ጉደኞቹ ጋር በመሆን የሲዳምኛ ፍደል በላቲን በመቅረX ዛሬ የሲዳማ ክልሉ የማንነቱ መግለጫ የሆነውን ሲዳሙ አፎ መሰረት ከመጣል ባሻገር እውን እንድሆን ፈር ከቀደዱ ምሁራን አንዱ ነው። ዳንኤል ከ1984᎐1986 ደቡብ ክልል ሥመሰረት የደቡብ ክልል የትምህርት ቢሮ ሃላፍ ሆኖ ለሶስት አመት ሰርቶአል።ከዚያም በአዋሳ መምህራን ኮሌጅ በሳይንስ መምህርነት፡ ቀጥሎም አዲስ ከተማና ፉራ ሞደል ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች በሳይንስ መምህርነት ሰርተዋል። ዳን ኤል የስባት ልጆች አባት ሲሆን በ71 አመቱ በአደረበት ድንገተኛ ህመም ከዝህ አለም በሞት ተለይቶአል።

ከዳንኤል ተማሪዎች የተሰጠ አስተያየት

==================

“ዓለም እውነተኛ የማስተማር ጥበብ አጥታለች! ለሙያህ እና ለተማሪዎችህ ያደረከው ቁርጠኝነት በእውነት አስደናቂ ነበር። የእርስዎ የማስተማር ፍቅር ለትውልድ ተላላፊ ነበር እናም በመማር እንድንወድ አድርገሃል። በቃላት ሊገለጽ በማይችል መልኩ ልባችንን ነክተሃል። ነፍስህ በገነት በሰላም ትረፍ “